የማነ ንጉሥ ተገደሉ

Yemane Niguse

አብረዋቸው ሁለት የሠራዊቱ አባላት ተገድለዋል

ኢዛ (እሁድ የካቲት ፲፬ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. February 21, 2021)፦ ሕወሓትን በመቃወም የሚታወቁትና “ፈንቅል” በመባል የሚታወቀውን የተቃውሞ እንቅስቃሴ በሊቀመንበርነት በመምራት የሚታወቁት የማነ ንጉሥ የተገደሉት ከመቀሌ በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኘው ሔዋኔ ከተማ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያ በ12 ዓመት ለነዳጅ ግዥ ከግማሽ ትሪሊዮን ብር በላይ ወጪ አድርጋለች

Petroleum

አገሪቱ ከምታገኘው የውጭ ምንዛሪ ገቢ ላይ ግማሹ ለነዳጅ ግዥ ይውላል

ኢዛ (እሁድ የካቲት ፯ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. February 14, 2021)፦ የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ወጪ ከሚያወጣባቸው ምርቶች መካከል አንዱ ለኾነው ለነዳጅ ግዥ ባለፉት 12 ዓመታት ከግማሽ ትሪሊዮን ብር በላይ ብር ወጪ አውጥቷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሕወሓትን የጁንታ ቡድን አመራሮች ለሚጠቁም 10 ሚሊዮን ብር ሽልማት ተዘጋጀ

ሌተናል ጄኔራል አስራት ዴኔሮ

የጠቋሚዎች ማንነት የማይገለጽና በምስጢር እንደሚያዝ ተገልጿል

ኢዛ (ዓርብ ታኅሣሥ ፱ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. December 18, 2020)፦ የሕወሓት ጁንታ አመራሮች የሚገኙበትን ለጠቆመ ማንኛውም ዜጋ የ10 ሚሊዮን ብር ሽልማት የሚሰጥ መኾኑን የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኬሪያ ኢብራሒም እጅ በመስጠት የመጀመሪያ ኾኑ

ኬሪያ ኢብራሒም

የእስር ማዘዣ ከወጣባቸው 46 የሕወሓት ከፍተኛ ባለሥልጣናት አንዷ ነበሩ

ኢዛ (ማክሰኞ ኅዳር ፳፪ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. December 1, 2020)፦ የሕወሓት ጁንታ ቡድን አባልና በሕግ ሲፈለጉ የነበሩት የቀድሞ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሒም እጅ በመስጠት የመጀመሪያዋ ኾኑ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዳዲስ እና ያልተነገሩ ሚስጥሮች ይፋ የኾኑበት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ እያነጋገረ ነው

PM Abiy Ahmed speaks during a question and answer session with Parliament members in Addis Ababa, Ethiopia, November 30, 2020

ሕወሓት ዶ/ር ዐቢይ ጠ/ሚኒስትር ከኾኑ በኋላ ወደ ቢሮም ኾነ ወደ መኖሪያ ቤታቸው እንዳይገቡ ይከለክላቸው እንደነበር ይፋ አደረጉ

ኢዛ (ሰኞ ኅዳር ፳፩ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 30, 2020)፦ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ኾነው ከተሾሙ ዕለት ጀምሮ በሕወሓት ቡድን በተለያዩ ክልከላዎች ሲያደረግባቸው እንደነበርና፣ ወደ ቢሮና ወደ ቤት እንዳይገቡ ክልከላ ሲፈጽምባቸው የነበረ መኾኑን አስታወቁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

መከላከያ ሠራዊቱ መቀሌን ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጠረ

Gen. Berhanu Julla and PM Abiy Ahmed

“የትግራይ ሕዝብ ከጁንታው ጋር ያለመኾኑን አስመስክሯል” ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ

ኢዛ (ቅዳሜ ኅዳር ፲፱ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 28, 2020)፦ የመከላከያ ሠራዊቱ መቀሌን ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠሩን ተገለጸ። ጠቅላይ ሚስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የትግራይ ሕዝብ ከስግብግቡ ጁንታ ጋር አለመኾኑን በተግባር ማስመስከሩንና በዚህ ዘመቻ ንጹኀን ዜጎች ዒላማ ሳይኾኑ ከተሞችንና ቅርሶቻችን ሳይጎዱ መቀሌ ለመግባት መቻሉንም አስታወቁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሕዝብን ያስቆጣውና በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተገኘው የጦር መሣሪያ

የሕወሓት ጁንታ ቡድን በአዲ ምስኖ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያከማቻቸው የጦር መሣሪያዎች

የተገኙት የመድፍ ጥይቶችና የቢኤም መሣሪያዎች ናቸው

ኢዛ (ቅዳሜ ኅዳር ፲፱ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 28, 2020)፦ ዛሬ ኅዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም. የአገር መከላከያ ሠራዊት የመረጃ ገጽ ይፋ እንዳደረገው፤ መረጃው በራያ ግንባር አካባቢ የሕወሓት ጁንታ ቡድን በአዲ ምስኖ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ብዛት ያላቸው የጦር መሣሪያዎች አከማችቶ እንደነበር ገልጿል። ይህም ሕዝቡን አስቆጥቷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ለሁለተኛ ጊዜ የሕወሓት ሮኬቶች ወደ አስመራ ተተኩሰዋል

Asmara

በመኖሪያ አካባቢዎች ላይ አርፈዋል

ኢዛ (ዓርብ ኅዳር ፲፰ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 27, 2020)፦ የሕወሓት ጁንታ ቡድን ከደቂቃዎች በፊት ወደ አስመራ የተለያዩ ከተሞች ሮኬቶችን ተኩሷል። ሮኬቶቹ የመኖሪያ አካባቢዎች ላይ ያረፉ ሲሆን፤ ስላደረሱት ጉዳት ገና በመጣራት ላይ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

መቀሌና ጁንታው በጥቂት ቀናት እንደሚያዙ ተገለጸ

ሌተናል ጄኔራል ሐሰን ኢብራሒም

ሠራዊቱ መቀሌን ለመቆጣጠር ስትራቴጂክ ቦታ ይዟል
በሁሉም ግንባር ሠራዊቱ ድል ማድረጉንና የቀረው መቀሌ ብቻ ነው

ኢዛ (ዓርብ ኅዳር ፲፰ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 27, 2020)፦ የአገር መከላከያ ሠራዊት መቀሌን እና የወንጀለኛውን ጁንታ ቡድን አባላት ለመቆጣጠር የሚያስችሉትን ስትራቴጂክ ቦታዎችን መያዙንና በጥቂት ቀናት ውስጥ የጁንታውን አባላት ለሕግ የሚያቀርቡ መኾኑን ሌተናል ጄኔራል ሐሰን ኢብራሒም አስታወቁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!