ስብኃት ገብረእግዚአብሔር ስለሁለተኛ ትዳሩ እንዲህ ብሎ ነበር

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

Sebhat Gebregziabher”ሶቅራጥስ ፈላስፋ ነው። ሚስቱ ደግሞ ጨቅጫቃ ነች። አንዳንዴ ወይዘሮ ይሉኝታና አቶ ይሉኝታ ቢስ ይጋባሉ። ሶቅራጥስ ሲፈላሰፍ ነው የሚውለው። ትዳርዋን ለምትወድ ሴት ደግሞ ይህ ዓይነቱ አካሄድ የሚጥም ሕይወት አይደለም። የሶቅራጥስ ሚስት ሲበዛ ጨቅጫቃ ነበረች።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

”ከአስሩ ስምንቱ መንጋ ናቸው” ስብኃት ገብረእግዚአብሔር

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

”ከአስር ሰዎች መካከል አንዱ በውድም በግድም አብረውት ያሉትን ሰዎች መምራት ነው የሚፈልገው። ሌላኛው ሰውዬ መምራትም መመራትም አይፈልግም። አፈንጋጭ ነው። ፈላስፋ፣ ሳይንቲስት፣ ደራሲ፣ ወይም የአንድ ጥበብ ሊቅ ነው። ሁሌም ራሱን እንጂ ሌሎችን አያያቸውም። አብረውት ቢኖሩም፣ ባይኖሩም ሁሌም ብቻውን ነው። የተቀሩት ስምንቶቹ ግን መንጋ ናቸው።” ስብኃት ገብረእግዚአብሔር

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከ"ድርጅታዊ ምዝበራ" መጽሐፍ ላይ የተወሰደ ማስታወሻ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

"ድርጅታዊ ምዝበራ" በዶ/ር አክሎግ ቢራራገለታው ዘለቀ

በቅርቡ ለንባብ የበቃው "ድርጅታዊ ምዝበራ" የተሰኘው መጽሐፍ ደራሲ ዶክተር አክሎግ ቢራራ ጎንደር ተማሪ በነበሩበት ወቅት በአንድ ነገር ተመስጠው ነበር። ይህ ምናባቸውን የገዛው ነገር በጎንደር ውስጥ እድሜው የትየለሌ የሆነ የአንድ የዋርካ ዛፍ ተፈጥሮ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዶ/ር አበራ ጀምበሬ ትዝታዬና መጽሐፉ

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive
ዶ/ር አበራ ጀምበሬ
ዶ/ር አበራ ጀምበሬ

ከመዝገብ ቤት ሠራተኛነት እስከ ሚንስትሮች ምክር ቤት ዋና ጸሐፊነት

ወለላዬ (ከስዊድን)

ዛሬ ብቻ ኖረው - በዛሬ ያልቀሩ

ነገንም አስበው - ለነገ የሠሩ
ለራሳቸው ሳይሆን - ለህዝብ የኖሩ
ግዴታ ሆነና ሞት - ቢሆን ዕጣቸው
ሲበራ ይኖራል - አይጠፋም ሐቃቸው

ግጥም - አስራት ዳምጠው

በስድስተኛ ዓመቴ መጨረሻ ግድም አንድ ቀይ እንግዳ እቤታችን መጣ። ከናትና አባቴ ጋር ሆኜ ከሰውየው ጋር የመቀመጥ እድል አገኘሁ። ቀዩ ሰውዬ ሳቂታ ፊት፣ የሚቁለጨለጩ አይኖች፣ ሰልካካ አፍንጫና፣ የሞሉ ጉንጮች አሉት።ያም ሆኖ ሙሉ ፊቱ ስትታይ አነስተኛ ነች።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የመቀሌ ጥንታዊ ቀልዶች (ተስፋዬ ገብረአብ)

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

ተስፋዬ ገብረአብ (“እፍታ - ቅፅ አንድ” (1991) መጽሐፍ)

በመቀሌ ከተማ የቀልድ ነገር ሲነሳ፣ ካሳ ደበስ እና አስፋቸው ፈቃዱም አብረው ይነሳሉ። በእነዚያ የሩቅ ዘመናት ከማለዳው አራት ሰአት ጀምሮ የጠላ ገበያ ይደራባት በነበረችው መቀሌ ቀልድ ትልቅ ስፍራ ይሰተው ነበር። ጥርስ የማያስከድኑ ቀልዶችም በጠላና በአረቄ ቤቶች ይንቆረቆራሉ። ሁለቱ የቀልድ አባቶች ዛሬ በህይወት ባይኖሩም፣ ከተማይቱ ነዋሪዎች ግን ዛሬም ድረስ በፈገግታ ያነሳሱዋቸዋል። በአማርኛ ሲቀርቡ ያስቁ ይሆን?

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!