ከጥር 5 እስከ 6 ቀን 2009 ዓ.ም (ጃንዋሪ 13-14) በዋሽንግተን ዲሲ የተካሄደው ሁሉን አቀፍ የምክክር ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ
የአገር አድን የቀውጢ ጊዜ ግብረ ኃይል ተቋቋመ፤ ሁነኛ የአንድነት ኃይሎች አማራጭ በአጭር ጊዜ የማውጣት ሂደት ላይ ስምምነት ተደረሰ

አዘጋጅ የሆኑት ሶስት ድርጅቶች (ሸንጎ፣ የሽግግር ምክር ቤትና የወጣቶች ንቅናቄ) ቀደም ሲል ሲያደርጉት የነበረውን ግንኙነት በማደስ ላለፉት 7 ወራት ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር ተከታታይ የሁለትዮሽ፤ የወል ግንኙነቶችን እና ጥረቶችን በማድረግ ከቆዩ በኋላ፤ በአገራችን ጉዳይ ላይ ባለ ድርሻ ለሆኑ ለሁሉም የፖለቲካና የሲቪክ ድርጅቶች ኦፊሽያል ጥሪ በማድረግ እንደሚገኙ በደብዳቤ ካረጋገጡት 10 ድርጅቶች መካከል 9ኙ በጥር 5 እና 6 ቀን 2009 ዓ፡ም (ጃንዋሪ 13 - 14 ቀን 2017) ተገኝተው የተሳካ ጉባዔ በዋሺንግተን ዲሲ አካሂደዋል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
“እንኳን በሳይበር የሚደረግ ጥቃት ይቅርና የወያኔ ተገንጣይ መንግስት እስር ቤትም ከዓላማችን አላሰናከለንም” - ከዘ-ሐበሻ የተሰጠ መግለጫ


