ከኢዜማ መሪ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የተላለፈ መልዕክት

ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ፤ እንደምን ከረማችሁ
በዛሬው ዕለት እንደ ኢዜማ መሪም ሆነ እንደ አንድ ዜጋ፣ ከኢትዮጵያውያን ወገኖቼ ጋር በዚህ መልክ ለመገናኘት ምክንያት የሆነኝ ከፊታችን በተደቀነው ምርጫ ላይ ኢዜማን እንድትመርጡ ለመቀስቀስ አይደለም። እሱ ሁሉም የፖለቲካ ድርጅቶች የምርጫው ቅስቀሳ ጊዜ በግልጽ ሲታወጅ የምናደርገው ይሆናል። ይልቁንም ዛሬ ላዋያችሁ የምፈልገው እንደ አገርም እንደ ሕዝብም ልንጋፈጠው የሚገባን ፊት ለፊታችን የተጋረጠ አንድ ትልቅ እውነትን ነው፤ ... ዛሬ በተለያዩ የአገራችን አካባቢዎች የሚከሰቱ አለመረጋጋቶች፣ ግጭቶችና ከዕለት ወደ ዕለት አሳሳቢ እየሆነ የመጣው የሰላም ዕጦት፣ ነገ ደግሞ ምን ይዞ ይመጣ ይሆን የሚል ሥጋት/ጭንቀት አለ።

በየሜዲያው የሚወጡ፤ የተጨበጡና ያልተጨበጡ ሁላችንንም የሚያስጨንቁ በርካታ መረጃዎችን እንሰማለን። ተማሪዎች ታገቱ/ተገድሉ፥ መስጊድና ቤተ-ክርስቲያን ተቃጠሉ፥ ባንኮች ተዘረፉ፥ መንገድ ተዘጋ፥ ንብረት ተዘረፈ ወይም ወደመ፣ የሚሉ ዜናዎችን መስማት ከምንግዜውም በላይ እየተለመደ ነው። ከመደበኛ ስራችን ውጭ በተለያዩ ማህበራዊ ስብስቦች ስንገኛኝ የምንወያያቸው ጉዳዮች ለመሆኑ አገራችን ወዴት እየሄደች ነው? በዚህ በምናየውና በምንሰማው ሁኔታ ከቀጠልን እንደ አገር መቀጠል እንችላለን ወይ? ከዚህ ከገባንበት አዘቅት መቼና እንዴትስ ነው የምንወጣው? የኛም ሆነ የልጆቻችን ዕጣ ፈንታስ ምን ይሆናል? የሚሉና ሌሎችም ብዙ ይህ ትውልድ ወደደም ጠላ መመለስ ያለባችው አንኳር አገራዊ ጥያቄዎች፤ አዋቂና ህጻን ሳይለይ ሁላችንንም ከምንም በላይ ያስጨነቁና እንቅልፍ እየነሱ የሚገኙ ጥያቄዎች ሆነዋል። ... (ሙሉውን መልእክት በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ይጫኑ!)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!