የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት

እያንዳንዱ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት የትኞቹ ሠራተኞቻቸው ከቤታቸው እንደሚሠሩ ይወስናሉ

ኢዛ (ማክሰኞ መጋቢት ፲፭ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 24, 2020)፦ የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች ከነገ መጋቢት 16 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ተጨማሪ ውሳኔ እስኪሠጥ ድረስ ሥራቸውን በቤታቸው ኾነው እንዲሠሩ ዛሬ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባካሔደው 17ኛ አስቸኳይ ስብሰባ ወሰነ።

ምክር ቤቱ የኮሮና ቫይረስ ሊያስከትል የሚችለውን ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ተጽእኖ ከግምት በማስገባት የተወሰደ ውሳኔ ነው ተብሏል። ከቤታቸው ኾነው የሚሠሩት የመንግሥት ሠራተኞች የትኞቹ (እነማን) እንደኾኑ የሚወሰነው በእያንዳንዱ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤት በሚወጣ ደንብ መሠረት እንደኾነ ታውቋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ የ17ኛውን አስቸኳይ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ውሳኔዎችን በሚመለከት ይፋ ያደረገው ሙሉ መግለጫ ከዚህ በታች ያገኙታል። (ኢዛ)

የጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ የ17ኛውን አስቸኳይ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ውሳኔዎችን በሚመለከት ይፋ ያደረገው ሙሉ መግለጫ
የጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ የ17ኛውን አስቸኳይ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ውሳኔዎችን በሚመለከት ይፋ ያደረገው ሙሉ መግለጫ

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!