Total coronavirus cases in Ethiopia, June 9, 2020

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የሁኔታ መግለጫ (ማክሰኞ ሰኔ 2 ቀን 2012 ዓ.ም.)

የሟቾች ቁጥር ወደ 32 ከፍ ብሏል

ኢዛ (ማክሰኞ ሰኔ ፪ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. June 9, 2020)፦ በኢትዮጵያ በ24 ሰዓታት ውስጥ 190 የሚኾኑ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሪፖርት ተደረገ።

ዛሬ ማክሰኞ ሰኔ 2 ቀን 2012 ዓ.ም. ይፋ በተደረገው የጤና ሚኒስቴር ዕለታዊ ሪፖርት 4,599 የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው ሰዎች 190ዎቹ በቫይረሱ መያዛቸው ታውቋል። ይህም ባለፉት ሦስት ወራት በአንድ ቀን ከፍተኛ ቁጥር የተገኘበት ዕለት አድርጎታል።

ከ190ዎቹ ውስጥ 153 የሚኾኑት የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በመኾናቸው በአዲስ አበባ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር ከዕለት ዕለት እየጨመረ መምጣቱን የሚያሳይ ኾኗል። በዛሬው ዕለት ቀሪዎቹ ተጠቂዎች 16 ከኦሮሚያ፣ አሥር ከአማራ፣ ሦስት ከሐረሪ፣ ሦስት ከሶማሌ፣ ሦስት ከደቡብና ሁለት ከትግራይ ክልሎች መኾናቸው ታውቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ባለፉት 24 ሰዓታት አምስት ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተው በመሞታቸው አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 32 ደርሷል። እስካሁን በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥርም 2,336 መድረሱን ሪፖርቱ አመልክቷል።

በአንድ ቀን ውስጥ 18 ሰዎች ያገገሙ በመኾኑም፤ አጠቃላይ ያገገሙ ሰዎችን ቁጥር ወደ 379 ከፍ አድርጎታል። በኢትዮጵያ እስካሁን ምርመራ የተደረገላቸው ሰዎች ቁጥር ደግሞ 152,334 ነው። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!