ወደ ሱዳን ሊወጣ የነበረ 150 ሺሕ ዶላር ተያዘ

የአሜሪካ ዶላር
የብር ኖት ለውጡን ተከትሎ በኬላዎች የሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር ቁጥጥሩ ጨምሯል
ኢዛ (እሁድ መስከረም ፲ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. September 20, 2020)፦ ከኢትዮጵያ በመተማ በኩል ወደ ሱዳን ሊወጣ የነበረ 150 ሺሕ ዶላር በመተማ ጉምሩክ በተደረገ ፍተሻ ተያዘ።
የመተማ ዮሐንስ አስተዳደር ፖሊስ ዛሬ እንዳስታወቀው፤ በኢትየጵያና ሱዳን ድንበር አካባቢ በሕገወጥ መንገድ ሊወጣ የነበረውን ዶላር የያዘው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት ነው።
የብር ኖት ለውጡን ተከትሎ ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውርን ለመቆጣጠር በተለያዩ ኬላዎች ቁጥጥሩ ጠብቋል። የመተማ ዮሐንስ ከተማ አስተዳደር ለሱዳን የሚዋሰን በመኾኑ፤ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡም ከአገር የሚወጡም ሕገወጥ ገንዘቦችንና ሌሎች ድርጊቶችን በጥብቅ እየተቆጣጠረ ነው ተብሏል። (ኢዛ)