አቶ መለስ ዓለም

አቶ መለስ ዓለም

ከሕወሓት በስተቀር የኢሕአዴግ ፓርቲዎችና አጋሮቹ ውሕደቱን ደግፈዋል

ኢዛ (ሐሙስ ኅዳር ፬ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. November 14, 2019)፦ የኢሕአዴግ አባል ድርጅቶችንና አጋር በሚል ይታወቁ የነበሩ ፓርቲዎችን በማዋሐድ አንድ ሕብረብሔራዊ ፓርቲ ለማድረግ ሲካሔድ የቆየው ዝግጅት መጠናቀቁ ታወቀ።

የኢሕአዴግ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊን ጠቅሶ ዛሬ ኢዜአ እንደዘገበው፤ ሕብረብሔራዊ ፓርቲ ለመመሥረት ሲደረግ የነበረው ዝግጅት ተጠናቅቋል።

ምክትል ኃላፊው አቶ መለስ ዓለም፤ “የኢሕአዴግ አባልና አጋር ድርጅቶችን በማዋሐድ አገራዊ ራዕይ ያለው ፓርቲ የመፍጠሩ ዝግጅት ተጠናቅቋል” በማለታቸውን ዘግቧል።

ከዚህ ይፋዊ መረጃ ቀደም ብሎ ከሕወሓት በስተቀር የኢሕአዴግ አባል ድርጅቶችና አጋር ድርጅቶች በሙሉ ውሕደቱን ደግፈው በተከታታይ መረጃ ሲሠጡ ቆይተዋል።

ይህ የኢሕአዴግ የውሕደት ጉዳይ ሰሞኑን በሚካሔደው የግንባሩ ስብሰባ ላይ ውሣኔ ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!