አዳነች አቤቤ

ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

የ33ቱ ተጠርጣሪዎች ክስ ተቋረጠ፤ ጋዜጠኛ ፍቃዱ በይቅርታ ይለቀቃል

ኢዛ (ረቡዕ መጋቢት ፲፮ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 25, 2020)፦ የፌዴራሉ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የኮሮና ቫይረስ ሥርጭትን ለመከላከልና ለመግታት ሲባል ከአራት ሺህ በላይ ታራሚዎች በይቅርታ፣ እንዲሁም 33 ግለሰቦች ደግሞ ክሳቸው ተቋርጦ እንደሚለቀቁ አስታወቀ። በይቅርታ ከእስር ከሚፈቱት ውስጥ ጋዜጠኛ ፍቃዱ ማኅተመወርቅ ይገኝበታል።

በይቅርታ ከእስር ከሚለቀቁት ውስጥ እስከ ሦስት ዓመት በሚያስቀጣ ቀላል የወንጀል ዐይነቶች የፍርድ ውሳኔ ያገኙ ሁሉም ታራሚዎች፣ የእስር ቆይታቸውን በማጠናቀቅ ላይ ያሉና በሕጉ መሠረት ለመፈታት አንድ ዓመት የቀራቸው ሁሉም ታራሚዎች እንደሚለቀቁ አዲሷ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ዛሬ መጋቢት 16 ቀን 2012 ዓ.ም. በሠጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

ከግድያ ወንጀል ሌላ በሌሎች ወንጀሎች የፍርድ ውሳኔ ያገኙ፣ ከሕፃናት ጋር ማረሚያ ቤት የሚገኙና ነፍሰጡር መኾናቸው የተረጋገጠ ሁለት ሴት ታራሚዎችም ይለቀቃሉ ተብሏል።

ከግድያ ወንጀል ውጭ በሌሎች ወንጀሎች የፍርድ ውሳኔ ያገኙ የውጭ ዜጋ የኾኑ ታራሚዎችም እንደሚፈቱ ታውቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ ፍቃዱ ማኅተመወርቅ ከእስር እንደሚለቀቅ ታውቋል። የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በፌስቡክ ገጹ የሚከተለውን መረጃ አስተላልፏል።

“የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ዛሬ በሠጡት መግለጫ በመንግሥት በኩል የፖለቲካ ምኅዳሩን ለማስፋት እየሠራቸው ካሉ በርካታ ሥራዎች ጋር በተያያዘ የጋዜጠኛ ፍቃዱ ማኅተመወርቅ ክስ እንዲቋረጥ መወሰኑን ገልጸዋል።

“ጋዜጠኛው ለአንድ ዓመት በማረሚያ ቤት የቆየ መኾኑን የገለጹት ክብርት ዓቃቤ ሕጓ ለውጡን ተከትሎ የመጣውን የመናገር ነፃነት ለማረጋገጥና የነበሩ ችግሮችን ለመቅረፍ እንዲያስችል ሲባል መንግሥት የሕግ የበላይነትን ለማስጠበቅ እና የፍትሕ ሥርዓቱን ተገማች በማድረግ ትኩረት አድርጎ በርካታ ሥራዎችን ሲሠራ መቆየቱንና ለዚሁ ሲባል የጋዜጠኛው ክስ መቋረጡን ጠቁመዋል። በለውጡ ማግሥት መንግሥት በምሕረት አዋጁ በርካታ ጋዜጠኞች፣ ብሎገሮችና የሚዲያ ተቋማት ክሳቸዉ ተቋርጦ እንዲፈቱ ማድረጉ የሚታወስ ነው።

ስለጋዜጠኛ ፍቃዱ ማኅተመወርቅ ዓቃቤ ሕግ “ለአንድ ዓመት በማረሚያ ቤት ቆየ” በማለት የሠጠው መረጃ ትክክለኛ አይደለም። ጋዜጠኛ ፍቃዱ በእስር የቆየው ላለፉት 5 ወራት ከአምስት ቀን ሲሆን፣ ይህም ከጥቅምት 11 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ዛሬ መጋቢት 16 ቀን 2012 ዓ.ም. ነው። ጋዜጠኛ ፍቃዱ ተከስሶበት በነበረው ክስ፤ ጥቅምት 18 ቀን 2012 ዓ.ም. በልደታ ፍርድ ቤት ስምንተኛ ወንጀል በዋለው ችሎት “ጥፋተኛ” ተብሎ የሰባት ዓመት እስርና የሰባት ሺህ ብር ቅጣት ተጥሎበት እንደነበር አይዘነጋም።

ጋዜጠኛ ፍቃዱ ማኅተመወርቅ
ጋዜጠኛ ፍቃዱ ማኅተመወርቅ

ጋዜጠኛው የይግባኝ መብቱን በመጠቀም በጠበቃው በኩል ለልደታ ፍርድ ቤት 8ኛ ወንጀል ችሎት ይግባኙን አቅርቦ ጉዳዩን ሲከታተል እንደነበር ይታወቃል። ጋዜጠኛ ፍቃዱ ከነፃ ፕሬስ ምስረታ ጀምሮ በተለያዩ የነፃ ፕሬሶች ላይ ሲሠራ ቆይቷል። ለእስር የተዳረገውም ከስድስት ዓመት በፊት በከፈተው ክስ ሲሆን፤ ዓላማውም የነፃውን ፕሬስ በግብር ስም ማጥፋት እንደነበር ይታወቃል።

በዛሬው የዓቃቤ ሕግ መግለጫ 33 ተጠርጣሪዎች ክሳቸው እንዲቋረጥ የተደረገ መኾኑ አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ስም ዝርዝራቸውንና ምክንያቱን እንደሚከተለው ይገኛል። (ኢዛ)

መጋቢት 17 ቀን 2012 ዓ.ም ክስ የተቋረጠላቸው ግለሰቦች ስም ዝርዝር

ሀ. በሙስና ወንጀል በተባባሪነት ሚና የተከሰሱና ክሳቸው የተቋረጠው ከሕፃናት ጋር ማረሚያ ቤት የሚገኙ እና ነፈሰጡር መኾናቸው የተረገገጡ ሴቶች፤

1. ወ/ሮ ትዕግሥት ታደሰ
2. ሌ/ኮ ለተብርሀን ደሞዝ ተ/ሚካኤል
3. ወ/ሮ ፅጌ ተክሉ
4. ወ/ሮ ሶፊያ ኑሮ
5. ወ/ሮ ቅድስት አያሌው አባተ
6. ወ/ሮ እናኑ ፋንታሁን ባዩ
7. ወ/ሮ ሱመያ ሰይፉ ግባሽ

ለ. በተለያዩ የወንጀል ጉዳዮች በተባባሪነት ሚና ተከስሰው የሚገኙ ክስ የተቋረጠላቸው ሴቶች፤

1. ወ/ሮ ሙሊያ አብደላ ዑሰማን
2. ወ/ሮ ቤቴልሔም አወል አባፌጣ
3. ወ/ሮ መሰለች ታለዓን አሳየ
4. ወ/ሮ ሜላት ዘውዴ ማጫ

ሐ. በእነ ቢኒያም ተወልደማርያም መዝገብ ሙስና ወንጀል በተባባሪነት ሚና የተከሰሱና ክሳቸው የተቋረጠው፤

1. አቶ ይርጋም አብረሃ
2. አቶ ማስረሻ አሰፋ

መ. በአፋር የጨው ምርት ጋር በተያያዘ በእነ ሙሉጌታ ሰይድ መዝገብ የተከሰሱና ከዚህ ቀደም በዚሁ መዝገብ በከፊል ከተለቀቁት ጋር በተመሳሳይ መዝገብ ጉዳያቸው ሲጣራ የቆየ ከመኾኑ ጋር ተያይዞና የፍትሕ ሥርዓቱ ለሁሉም እኩል ተደራሽና ተገማች ለማድረግ ሲባል ክሳቸው የተቋረጠላቸው፤

1. ሐጂ ሰይድ ያሲንአቶ
2. ዶ/ር ሠይድ ኢሮ
3. አቶ ተፈሪ ዘውዴ
4. አቶ ወንዱአንተ ነጋሽ
5. አቶ አባይነህ ጥላሁን
6. አቶ ናደው ታደለ
7. አቶ ሀብቱ ሀጎስ
8. አቶ ይስማሸዋ ስዩም
9. አቶ ሳድቅ መሐመድ
10. አቶ አማረ አሰፋ
11. አቶ አረጋ አስፋው
12. አቶ መሐመድ አደም
13. አቶ ዋሴዕ ሳዲቅ
14. አቶ ያዮ ዋልህ ኢብራሂም
15. አቶ መሐመድ አኒሳ
16. አቶ ሰይድ ይማም
17. አቶ መህቡብ ማሄ
18. አቶ ወንድወሰን ማስረሻ
19. አቶ አብደላ ሙስጠፋ
20. አቶ ዋሴዕ አወል

ሠ. ከለውጡ በፊት በተከፈተበት መዝገብ ሲጣራ ቆይቶ ከውጭ አገር ሲመለሱ የፍርድ ውሳኔ የተሠጠው መኾኑ እና የፖለቲካ ምኅዳሩን ለማስፋት በተደረገው ማጣራት የይቅርታ ውሳኔ የተሠጠው፤

1. ጋዜጠኛ ፍቃዱ ማኅተመወርቅ

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ