ብልጽግና ፓርቲ

የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ

ኢዛ (ሐሙስ መጋቢት ፲፯ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 26, 2020)፦ የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት አመራሮች የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ለሚደረገው ጥረት የሚውል የአንድ ወር ደምወዛቸውን መለገሳቸውን አስታወቁ።

ፓርቲው አያይዞ እንደገለጸው የአንድ ወር ደምወዛቸውን የለገሱት የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት አመራሮች 50 ናቸው። በአሁኑ ወቅት ኮሮናን ለመከላከል ለሚያስፈልገው ዝግጅት በተለያየ መልኩ እየተካሔደ ሲሆን፤ ለዚህ የተቋቋመው ብሔራዊ ኮሚቴ ይፋ ሲደረግ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድና ሌሎች የብልጽግናና የመንግሥት አመራሮች የአንድ ወር ደምወዛቸውን መሥጠታቸውን በመግለጽ የገቢ ማሰባሰቡ ሥራ መጀመሩ ይታወቃል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!