ሕግ በተላለፉ ከ25 ሺህ በላይ የሚኾኑ የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገለጸ
የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር
ሰዎች የሚሰበሰቡባቸው የንግድ ድርጅቶች በሽታው በቁጥጥር ስር እስኪውል ድረስ ተዘግተው ይቆያሉ
ኢዛ (ረቡዕ መጋቢት ፴ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. April 8, 2020)፦ ከኮሮና ቫይረስ መከሰት ጋር ተያይዞ ፍትሐዊ ግብይት ለማስፈንና ያልተገባ የዋጋ ጭማሪን ለመቆጣጠር የተቋቋመው ብሔራዊ የገበያ ማረጋጋት ግብረኃይል ከ25 ሺህ በላይ ሕግ የተላለፉ የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ እንደወሰደ ገለጸ።
ብሔራዊ ግብረኃይሉ ዛሬ መጋቢት 30 ቀን ስንዳሳወቀው በአገር አቀፍ ደረጃ እርምጃ ከተወሰደባቸው 25,300 የንግድ ድርጅቶች ውስጥ በ1,684ቱ ላይ ክስ የተመሠረተ ሲሆን፤ 153 የሚኾኑ የንግድ ባለቤቶች በእስራት እንዲቀጡ መደረጉን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ምንም ዐይነት ኢኮኖሚያዊ ምክንያት ሳይኖር የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎችና አምራቾ ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ የተወሰደ መኾኑም ተገልጿል።
እንደከረምቦላ፣ ፑል፣ መጠጥና ጭፈራ ቤቶች እና ብዙ ሰዎች የሚሰበሰቡባቸው የንግድ ድርጅቶች በሽታው በቁጥጥር ስር እስኪውል ድረስ ተዘግተው ይቆያሉ ተብሏል። (ኢዛ)



