አብርሃ ደስታ

የዓረና ትግራይ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ አብርሃ ደስታ

ሙከራውን ያደረጉት የደኅንነት ሰዎች እንደኾኑ በአካባቢው የነበሩ ገለጹ

ኢዛ (ሰኞ ግንቦት ፲፯ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. May 25, 2020)፦ የዓረና ትግራይ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ አብርሃ ደስታ በትግራይ ክልል ደኅንነት አባላት ሊታፈኑ እንደነበር ተጠቆመ።

ትናንት እሁድ ግንቦት 16 ቀን 2012 ዓ.ም. 11፡30 ሰዓት አካባቢ በመቀሌ ከተማ ተደረገ የተባለው አፈና፤ በቀበሌ 18 ሊፈጸም የነበረ እንደኾነ የዓረና አመራር አምዶም ገብረሥላሴ በመረጃ ገጻቸው ላይ አስፍረውታል።

በአቶ አብርሃ ደስታ ላይ ዶልፊን ተሽከርካሪ በመያዝ ሙከራ ያደረጉት ሰዎች ማንነትን “ምንነታቸው ያልታወቁ” በሚል የገለጹት አቶ አምዶም፤ በአካባቢው ከነበሩ ሰዎች ማረጋገጥ የተቻለው፤ ሰዎቹ የደኅንነት አባላት መኾናቸውንና ተሽከርካሪዋም የደኅንነት መሥሪያ ቤቱ እንደኾነች እንደገለጹላቸው ጠቁመዋል።

አቶ አምዶምም ከቀናት በፊት ወደ ቤታቸው እንዳይገቡ ታግተው እና በቁጥጥር ስር ውለው እንደነበር መገለጹ አይዘነጋም። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!