ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ሕብረት 19 ቢሊዮን ብር ድጋፍ አገኘች
የአውሮፓ ሕብረት
ድጋፉ ከጤናና ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ የሚፈጠር ኢኮኖሚያዊ ቀውስን ለመከላከል የሚውል ነው
ኢዛ (ሰኞ ሰኔ ፰ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. June 15, 2020)፦ የአውሮፓ ሕብረት እና አባል አገራቱ የኢትዮጵያን የጤና ሥርዓት ለማጠናከር፣ ለለይቶ ማቆያና የማኅበራዊ ጥበቃ ሥርዓቱን ለማጠናከር እና ለተያያዥ ክንውኖች የሚረዳ የ487 ሚሊዮን ዩሮ (19 ቢሊዮን ብር) ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ።
ሕብረቱ አዲስ አበባ በሚገኘው የመረጃ ገጹ እንዳመለከተው በኮሮና ወረርሽኝ ወቅት ለኢትዮጵያ በሰጠው ድጋፍ አጋርነቱን እያሳየ መኾኑን ገልጾ፤ ሕብረቱና አባል አገራቱ በዚህ ቀውስ ወቅት ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን ድጋፍ አጠናክረው መቀጠላቸውን ያሳያል ብሏል።
የገንዘብ ድጋፉ ከጤናና ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች የሚፈጠር ኢኮኖሚያዊ ቀውስን ለመከላከል የሚያስችል ስለመኾኑም መረጃው አመልክቷል። (ኢዛ)



