Ethio Telecom

ኢትዮ ቴሌኮም

የሽያጭ ሒደቱ አደጋ አለው ብሏል

ኢዛ (ቅዳሜ ሰኔ ፳ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. June 27, 2020)፦ ገዥው ፓርቲ የኢትዮ ቴሌኮምን ከፊል ይዞታ ለመሸጥ እየሔደበት ያለውን ጥድፊያ በመኮነን ይህንን ጥድፊያ በአስቸኳይ እንዲቆም ጠየቀ።

ኢዜማ በዚሁ የኢትዮ ቴሌኮም ከፊል ሽያጭ ጉዳይ ባወጣው መግለጫ በአገር ኢኮኖሚ ላይ ወሳኝ የሚለውን የቴሌኮም ኢንዱስትሪ እንዲህ በጥድፊያ ለመሸጥ የሚያደረገው ጥድፊያ አግባብ አለመኾኑን በመግለጽ፤ በዚህ ዙሪያ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች በአስቸኳይ ይቁም ብሏል።

ሽያጩ ፍጹም አደገኛና የአገርን ሕልውና አደጋ ላይ የሚጥል ጭምር መኾኑን የሚያመለክተው የኢዜማ መግለጫ፤ መንግሥት በዚህ ጉዳይ ላይ ቆም ብሎ ማሰብ እንደሚኖርበትም አሳስቧል።

ገዥው ፓርቲ ቅድሚያ ለሌሎች ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ጉዳዮች ይስጥ የሚል አንደምታ ያለው መልእክትም የያዘው የኢዜማ መግለጫ፤ በውጭ ጫና በሩጫ ቴሌን ለመሸጥ የሚደረገው ሒደት ሊቆም ይገባልም ብሏል። ኢዜማ በዚህ ጉዳይ ላይ ያወጣውን ሙሉ መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ!(ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!