የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ከኃላፊነታቸው ተነሱ

ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረሕይወት
ከኃላፊነታቸው የተነሱበት ምክንያት አልተገለጸም
ኢዛ (ሰኞ መስከረም ፬ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. September 14, 2020)፦ ከግንቦት 28 ቀን 2005 ዓ.ም. ጀምሮ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲን በፕሬዝዳንትነት ሲመሩ የቆዩት ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረሕይወት ከኃላፊነታቸው ተነሱ።
በአዲሱ የሣይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ ተፈርሞ በወጣው ደብዳቤ መሠረት ፕሮፌሰር ክንደያ ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንትነታቸው ከመስከረም 5 ቀን ጀምሮ መነሳታቸውን አስታውቋል።
ፕሮፌሰር ክንደያ ከኃላፊነታቸው የተነሱበት ምክንያት የሚኒስቴሩ ደብዳቤ ባይገልጽም፤ ላበረከቱት አስተዋጽኦ አመስግኗል። (ኢዛ)