Wegagen Bank

ወጋገን ባንክ

አዲሷ ፕሬዝዳንት በቅርቡ ሥራቸውን የጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል

ኢዛ (ረቡዕ ጥቅምት ፲፰ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 28, 2020)፦ የወጋገን ባንክ ፕሬዝዳንት ኃላፊነታቸውን ለመልቀቅ ባስገቡት የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤ መሠረት፤ ጥያቄያቸው ተቀባይነት አግኝቶ መሰናበታቸው ታወቀ።

ፕሬዝዳንቱ አቶ ዓባይ ማኅሪ ኃላፊነታቸውን ለመልቀቅ ያስገቡትን የመልቀቂያ ደብዳቤ ተቀብሎ ስንብቱን የፈቀደላቸው የወጋገን ባንክ ቦርድ መኾኑ ታውቋል።

አቶ ዓባይ ከኃላፊነታቸው ለመልቀቅ ውሳኔ ላይ የደረሱበት ምክንያት አልታወቀም። ኾኖም አቶ ዓባይን የሚተካ ፕሬዝዳንት ለመሾም ባንኩ አዲስ ፕሬዝዳንት ለማግኘት ሲያፈላልግ ቆይቶ፤ የእናት ባንክ ምክትል ፕሬዝዳንት በመኾን እያገለገሉ ያሉትን ወይዘሮ ብርቱካን ገብረእግዚን በማግባባት የወጋገን ባንክ ፕሬዝዳንት እንዲኾኑ ያቀረበላቸውን ጥያቄ ወይዘሮዋ ተቀብለዋል ተብሏል።

በዚህም መሠረት ወ/ሮ ብርቱካን እናት ባንክን ለቅቀው የወጋገን ባንክ ፕሬዝዳንት ኾነው አዲሱን ሥራቸውን ይጀምራሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው።

ወ/ሮ ብርቱካን የቀድሞው የሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩትና ሕወሓት ለሁለት በተከፈለበት ወቅት ከኃላፊነታቸው እንዲሰናበቱ የተደረጉት የአቶ ተወልደ ወልደማርያም ባለቤት ናቸው። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ