PM Abiy Ahmed

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ

ዋነኛ አጀንዳው ከትግራይ ክልል ሕግ ማስከበር ጋር እንደሚያያዝ ይጠበቃል

ኢዛ (እሁድ ኅዳር ፳ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 29, 2020)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በነገው ዕለት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመቅረብ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ እንደሚሰጡ ተመለከተ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በነገው (ሰኞ ኅዳር 21 ቀን 2013 ዓ.ም.) የምክር ቤቱ ሁለተኛ ልዩ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ከሚሰጡት ማብራሪያ በተጨማሪ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች መልስ ይሰጣሉ ተብሏል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመረጃ ገጹ ጨምሮ እንዳመለከተው በልዩ ስብሰባ አጀንዳዎች የምክር ቤቱ ስድስተኛ ዓመት የሥራ ዘመን አራተኛ ስብሰባ ቃለ ጉባዔ መርምሮ ያጸድቃልም ተብሎ ይጠበቃል።

የምክር ቤቱ ወቅታዊ አጀንዳ በትናንትናው ዕለት መጠናቀቁ የተገለጸው የትግራይ የሕግ ማስከበር ዘመቻ እንደሚኾን ይታመናል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ