የዓለም ሎሬት ዶክተር ጥበበ የማነብርሃን

የዓለም ሎሬት ዶክተር ጥበበ የማነብርሃን

ሕይወታቸው ያለፈው በኮቪድ 19 ነው

ኢዛ (እሁድ የካቲት ፲፬ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. February 21, 2021)፦ ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው የሕክምና ባለሙያዎች መካከል አንዱ የኾኑትና በአገር ጉዳዮች ተሳትፏቸው የሚታወቁት እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት ዶክተር ጥበበ የማነብርሃን አረፉ።

ከሚታወቁበት የሕክምና ሙያቸው ከ60 በላይ የምርምር ሥራዎችን በዓለም አቀፍ ጆርናሎች በማሳተም ጭምር ስማቸው የሚነሳው እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት ጥበበ የማነብርሃን የሕልፈት ዜናቸው የተሰማው በትናንትናው ዕለት (ቅዳሜ የካቲት 13 ቀን 2013 ዓ.ም.) ነው።

ሐኪም፣ ዲፕሎማት፣ ተመራማሪ፣ የአገር ሽማግሌ፣ አስታራቂ በመኾን አገራቸውን ሲያገለግሉ የቆዩት እኒህ ኢትዮጵያዊ፤ በሕይወት ዘመናቸው ላበረከቱዋቸው አገልግሎትና አስተዋጽኦዋቸው በዓለም አቀፍና በአገር ደረጃ የተለያዩ ሽልማቶች የተበረከቱላቸው ናቸው። በሐረር ከተማ የተወለዱት የዓለም ሎሬት ጥበበ ከ40 ዓመታት በላይ ትዳራቸው ሁለት ልጆችን አፍርተዋል።

በዓለም ሎሬት ሕልፈተ ሕይወት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ኀዘናቸውን የገለጹ ሲሆን፣ ሌሎች መንግሥታዊ ተቋማትና ታዋቂ ሰዎች በእኒህ ጉምቱ አገር አገልጋይ ኢትዮጵያዊ ሞት ኀዘናቸውን እየገለጹ ሲሆን፣ ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናትን እየተመኙ ነው።

የዓለም ሎሬት ጥበበ በኮቪድ 19 (ኮሮና) ምክንያት ሕይወታቸው ማለፉን የጤና ሚኒስትር ገልጿል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ