በትግራይ ክልል ከሚፈለጉ ተጠርጣሪዎች 270 ያህሉ ተይዘዋል
ሕወሓት በማይካድራ በፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀል ሰለባ የኾኑ
በማይካድራው ጭፍጨፋ ከተጠረጠሩት 137ቱ ፖሊስ እጅ ገብተዋል
ኢዛ (ሐሙስ መጋቢት ፱ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. March 18, 2021)፦ በትግራይ ክልል ከሕግ ማስከበር ዘመቻው ጋር በተያያዘ 270 የሚኾኑ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን እና በማይካድራው ጭፍጨፋ ከሚፈለጉት ውስጥም 137ቱን መያዙን የፌዴራል ፖሊስ ገለጸ።
የፌዴራል ፖሊስ የስምንት ወራት የሥራ አፈጻጸሙን በተመለከተ ዛሬ ሐሙስ መጋቢት 9 ቀን 2013 ዓ.ም. በሰጠው መግለጫ ላይ፤ በትግራይ ክልል ከሚፈለጉ ተጠርጣሪዎች 270 ያህሉን በቁጥጥር ሥር ያዋለ ሲሆን፤ ከእነዚህ ውስጥ 72ቱ የትግራይ ክልል አመራሮች የነበሩ ናቸው። በአሁኑ ወቅትም ወደ ማረሚያ ቤት እንዲወርዱ መደረጉም ተገልጿል።
በማይካድራ በንጹኀን ዜጎች ላይ ለደረሰው ጭፍጨፋ ይፈለጋሉ ከተባሉ 260 ተጠርጣሪዎች ውስጥ 137ቱ በቁጥጥር ሥር ስለመዋላቸው የሚያመለክተው የዛሬው መግለጫ፤ ቀሪዎቹ ከአገር በመሸሽ በሱዳን የስደተኞች መጠለያ ውስጥ ናቸው ተብሏል።
በሱዳን የስደተኞች መጠለያ የሚገኙትን ተጠርጣሪዎች ለመያዝ የሚያስችል እንቅስቃሴ እየተደረገ መኾኑን የፌዴራል ፖሊስ አስታውቋል። (ኢዛ)



