ኦነግ ሸኔ

የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች

የኦሮሞ ብልጽግና ፓርቲ በዚህ ጥቃት ዙሪያ መግለጫ አውጥቷል

ኢዛ (ቅዳሜ ሚያዝያ ፳፫ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. May 1, 2021)፦ በንጹሐን ግድያ በተደጋጋሚ እየተከሰሰ የሚገኘው የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ሲጓዙ ከነበሩ ተሳታፊዎች ላይ በከፈቱት ተኩስ 15 ሰዎችን ገድለዋል።

በትናንትናው ዕለት ከምዕራብ ጎጃም ዞን ቡሬ ወደ ነቀምቴ በሚጓዝ ተሽከርካሪ በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ግድያው የተፈጸመው በአማሮ ወረዳ ነው ተብሏል።

60 ተሳፋሪዎችን የያዘው የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ የዓባይ ወንዝን እንደተሻገረ ታጣቂዎች ተሽከርካሪውን በማስቆም፤ ተሳፋሪዎችን እንዲወርዱ በማድረግ ግድያውን ስለመፈጸማቸው ከጥቃቱ ያመለጡ ተሳፋሪዎች ገልጸዋል።

የወለጋ ዞን ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ብርሃኑ የባሳ በዚህ ጥቃት ዙሪያ እንደገለጹት፤ በተሳፋሪዎቹ ላይ ጥቃቱን ያደረሰው ኦነግ ሸኔ መኾኑንና ተሳፋሪዎችን በማስወረድ በ15 ሰዎች ላይ የግፍ ግድያ ተፈጽሟል ብለዋል።

በዚህ ጥቃት ሕይወታቸውን ካጡት መካከል የአማራ እና የኦሮሞ ተወላጆች እንደሚገኙበት ኮማንደር ብርሃኑ ገልጸዋል።

ታጣቂዎቹ ግልድያ የፈጸሙባቸው ተሳፋሪዎች ሌላ እስካሁን ቁጥራቸው በይፋ ያልገተለጹ ስለመቁሰላቸውም ለማወቅ ተችሏል።

በሊአላ በኩልም ጥቃቱ በተከፈተበት ወቅት የተወሰኑ ተሳፋሪዎች ወደ ጫካ ያመለጡ እና ሕይወታቸን ያተረፉ ሲሆን፤ አንዳንዶች ደግሞ በሕይወት ይኑሩ አይኑሩ ለማወቅ እንዳልተቻለ ታውቋል።

እንደ ኮማንደሩ ገለጻ ግን ከጥቃቱ የተረፉትን አሁንም የማፈላለግ ሥራ እየተሠራ መኾኑ ነው።

የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በተለያዩ አካባቢዎች ሲያደርሱ የነበረውን ጥቃት አውራ ጎዳና ላይ በማውጣት ተሽከርካሪ በማስቆም የፈጸሙት ጥቃትን በተመለከተ የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ድርጊቱን አውግዟል። ኦሮሞን እና አማራን ለማባላት የተሸረበውን እንዲህ ያለውን ጥቃት የሁለቱ ክልሎች ሕዝቦች የግል ጉዳይ ሳይኾን በኢትዮጵያ ላይ የታወጀ ከባድ ጦርነት መኾኑ ሊታወቅ እንደሚገባ አመልክቶ፤ በኦነግ ሸኔ ላይ እየተወሰደ ያለውን እርምጃ እንደሚቀጥል አስታውቋል።

ኦነግ ሸኔ ከክልሉ ጨረሶ ለማጥፋት ሕዝብ በሁሉም አካባቢ አንድነቱን አጠናክሮ የጸጥታ ኃይሉን እንዲደግፍ ጠይቋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!