ልጅ ዳንኤል ጆቴ

ልጅ ዳንኤል ጆቴ፣ የጥንታዊት ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ፕሬዝዳንት

“የውጭና የአገር ውስጥ ጠላቶ ቢተባበሩም ኢትዮጵያን ሊያቆስሏት ይችላሉ እንጂ፤ አያሸንፏትም” ልጅ ዳንኤል ጆቴ

ኢዛ (ሰኞ ሚያዝያ ፳፭ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. May 3, 2021)፦ ከነገ በስቲያ ረቡዕ ሚያዝያ 27 ቀን 2013 ዓ.ም. 80ኛ ዓመት የድል በዓልን (የአርበኞች ቀን) አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ የሰጡት የጥንታዊት ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ፕሬዝዳንት ኢትዮጵያ ከሰማንያ ዓመት በፊት የገጠማት የውጭ ወረራ የሚመስል ችግር እየገጠማት በመኾኑ ኢትዮጵያውያን በአንድነት ይቁሙ አሉ።

ፕሬዝዳንቱ ልጅ ዳንኤል ጆቴ ከሰማንያ ዓመት በኋላ ኢትዮጵያ እየገጠማት የውጭ ወረራ ችግርን ለመከላከልና ጠላቶችን ለማሸነፍ ኢትዮጵያውያን በአንድነት እንዲቆሙም አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ጠላቶች ኢትዮጵያን በዘር እና በሃይማኖት ሊከፋፍሏት በመጣደፍ በኃይል ሊያስፈራሩ እየሞከሩ ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ ጠላቶች ሕዝቡና መሪዎች እንዳይተማመኑ ሴራ እየጎነጎኑ እና እየሠሩ መኾኑንም በዛሬ መግለጫቸው ጠቁመዋል።

ኃያላን የሚባሉ መንግሥታት ሳይቀሩ ከአገር ጠላቶች ጎን እየታዩ ሲሆን፤ የአገር ውስጥ ባንዳዎችም አገር በማፍረሱ ሴራ ደጋፊ ኾነው መገኘታቸውን በመግለጽ፤ አገር ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ አመልክተዋል።

ይህም ቢሆን ግን የውጭና የአገር ውስጥ ጠላቶች ቢተባበሩም ኢትዮጵያን ሊያቆስሏት ይችላሉ እንጂ፤ እንደማያሸንፏት አመልክተዋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!