የአርበኞች ቀን

ምስጋና ለኢትዮጵያ አርበኞች (80ኛ ዓመት የአርበኞች ቀን በዓል፣ ሚያዝያ 27 ቀን 2013 ዓ.ም.)

"አሁን በኢትዮጵያ ላይ እየተቃጣ ያለውን ለኢትዮጵያ የሚደገስ የመከራ ድግስ መቀልበስ የሚቻለው ከተቀናጀን፣ ከተባበርን፣ ከተናበብን ነው" ጠ/ሚ/ር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ

ኢዛ (ማክሰኞ ሚያዝያ ፳፮ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. May 4, 2021)፦ አርበኞቻችን እንደነበሩበት ዘመን ዛሬም ኢትዮጵያ በውስጥ ባንዳዎችና በውጭ ጠላቶች ሙከራ እየተቃጣባት መኾኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን የገለጹት ነገ ሚያዝያ 27 ቀን 2013 ዓ.ም. የሚከበረውን 80ኛ ዓመት የአርበኞች ቀን በዓልን በማስመልከት ባስተላለፉት መልእክት ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው መልእክታቸው አሁን በኢትዮጵያ ላይ እየተቃጣ ያለውን ለኢትዮጵያ የሚደገስ የመከራ ድግስ መቀልበስ የሚቻለው ከተቀናጀን፣ ከተባበርን፣ ከተናበብን ነውም ብለዋል።

ይህንን ቀን ስናስብ ከጀግኖች አርበኞቻችን ሦስት ነገሮችን እየተማርን ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ እነዚህን ሦስት ነጥቦችም በዝርዝር አስፍረዋል። የመጀመሪያው ከምንም ነገር በላይ አገርን ማስቀደም ነው። ሁለተኛው ለአገር ማንንም አለመጠበቅ ሲሆን፤ ሦስተኛው ትልቅ ቁም ነገር አገርን የሚታደገው የዜጎች አንድነት መኾኑን አብራርተዋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!