Ahmedin Jebele

ኡስታዝ አሕመዲን ጀበል

በመጨረሻው ሰዓት ኡስታዝ አሕመዲን ራሱን ከምርጫ አገለለ

ኢዛ (ሰኞ ሰኔ ፯ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. June 14, 2021)፦ አንድ ሳምንት በቀረው ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ (ምርጫ 2013) ላይ በግል እንደሚወዳደሩ ካሳወቁት ታዋቂ ግለሰቦች መካከል የሚጠቀሱት ኡስታዝ አሕመዲን ጀበል ከምርጫው ራሱን እንዳገለለ አስታወቀ። እስካሁን ከምርጫውን ራሳቸው በኦፊሴል ያገለሉ እጩ ተወዳዳሪዎች ባላመኖራቸው፤ ኡስታዝ አሕመዲን ጀበል የመጀመሪያው እጩ ተወዳዳሪ ኾኗል።

ኡስታዝ አሕመዲን በመጨረሻው ሰዓት ከምርጫው ራሱን ለማግለል ውሳኔ ላይ የደረሰበትን ምክንያት በዝርዝር ማወቅ ባይቻልም፤ ዛሬ በፌስቡክ ገጹቸው በግል ምክንያቱ ከምርጫው መውጣቱን የሚያመለክት መልእክት አስፍሯል።

ይህም መልእክታቱ “ዘንድሮ በሚካሔደው ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ (ምርጫ 2013) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለጅማ ከተማ እንድወክላችሁ ሽማግሌ ከመላክ አንስቶ በተለያዩ መንገዶች እጩ እንድኾን በመጠየቅና ለእጩነት የሚጠበቀውን ፊርማ በራሳችሁ ተነሳሽነት በመፈረምና በማስፈረም የምርጫ ቅስቀሳ እንድጀምር፤ ለቅስቀሳውም “የሚጠበቅብንን ሁሉ ለመወጣት ከጎንህ ነን” በማለት ላሳደራችሁብኝ እምነትና አክብሮት ከልብ እያመሰገንኩ፤ በግል እጩነት ተመዘግቤ በነበረው በምርጫው በራሴ የግል ምክንያት ልቀጥል አለመቻሌን ላላሳወቅኳችሁ የጅማ ከተማ ነዋሪዎች ሳሳውቃችሁ ከታላቅ አክብሮት እና ይቅርታ ጋር ነው።” የሚል ነው።

በዘንድሮው ምርጫ ለመወዳደር ከተመዘገቡ እጩ ተወዳዳሪዎች ውስጥ እስካሁን በፓርቲም ኾነ በግለሰብ ደረጃ ከምርጫው ራሱን ማግለሉን ያስታወቀ ባለመኖሩ ኡስታዝ አሕመዲን እንዲህ ያለውን ውሳኔ በመወሰነ ብቸኛው እንደኾነ ይታመናል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ