አክቲቪስት ታማኝ በየነ፤ ከሰሞኑ "ዓላማችን ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር አፈራርሰን፤ ነፃ ኦሮሚያን መገንባት ነው!" ላሉት ወገኖች ብዙዎችን ያረካና ያስደሰተ ምላሽ የሰጠበት መድረክ፣ በእስራኤል።
በሎንዶን በተደረገ ውይይት ላይ፤ "ዓላማችን ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር አፈራርሰን፤ ነፃ ኦሮሚያን መገንባት ነው!" ሲሉ እነጃዋር መሐመድ ተደመጡ። ኢትዮሚዲያ ያቀናበረውን ቪዲዮውን ይመልከቱ!
ቪዥን ኢትዮጵያና ኢሳት ባዘጋጁት የውይይት መድረክ ላይ፤ አቶ አቻሜለህ ታምሩ ”ሽግግሩ ከአንድ የመከራ አዙሪት ወጥተን በአይነቱ ልዩ ወደሆነ ሌላ የመከራ አዙሪት የምንዘፍቅበት? ወይንስ ከታሪካዊ ችግሮቻችን የምንገላገልበት?” በሚል ርዕስ ላይ ያቀረቡትን ጥናታዊ ጽሑፍ ይህ ቪዲዮ ያሳያል።
አቶ አቻሜለህ በተለይ አቶ ጁነዲን ሳዶን አስመልክተው፤ በተለይም በደርግና በኃይሥላሴ ዘመን የነበሩትን የት/ቤቶች ቁጥርና የህዝብ ቁጥርን በተመለከተ በመረጃ በማስደገፍ፤ ”ኦሮሞው እንዳይማር ተደርጓል፣ አማራ ገዥ ነበር፣ ...” የሚባለውን የግራ ርዕዮተ ዓለም ፖለቲከኞችን ክስ ውድቅ ያደረጉበት ጥናታዊ ጽሑፍ ነው።
መጋቢ ቶሎሳ ጉዲሳ በወቅቱ የሀገራችን ጉዳይ ሰፋ ያለ ስብከት ለምዕመናን የሰበኩ ሲሆን፣ በሀገሪቷ ሠላም ይመጣ ዘንድ እስከ ኖቨምበር 12, 2016 እ.ኤ.አ. የሚቆይ ጾም ጠሎት አውጀዋል። በዚህ ወቅት ከኃይማኖት አባቶች የሚጠበቀውንና ብዙዎች ግን ለጉዳዩ ትኩረት ባለመስጠትም ሆነ በፍራቻ በዝምታ የተደበቡበትን የሀገሪቱን ችግርና የህዝብ ብሶት በተመለከተ፤ ዝምታውን ሰብረ ከወጡት የፕሮቴስታንት የኃይማኖት አባቶች ውስጥ መጋቢ ቶሎሳ ጉዲሳ አንዱ ናቸው። ይህን ቪዲዮ ይመለከቱት ዘንድ እንጋብዛለን። በዚህ አጋጣሚ ለመጋቢ ቶሎሳ ጉዲሳ ያለንን አድናቆትና ሀገር ወዳድነት ለማድነቅ እንወዳለን።
የኢትዮጵያውያን 2008 ዓ.ም. የዓመቱ ምርጥ ቀልድ ኹኖ ያገኘነው ይህ ቪዲዮ ሲሆን፣ ቀልደኛውም የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ናቸው።
ኢትዮጵያ ዛሬ
ክፍል ፩
ከዚህ በላይ ያለው ቪዲዮ የኢትዮጵያውያን ፎረም በአውሮፓ፤ በኔዘርላንድ ደን ሐግ ከተማ ጁላይ 29 ቀን 2016 እ.ኤ.አ. ባዘጋጀው ኮንፈረንስ ላይ፤ የተደረገ ህዝባዊ ውይይት ክፍል አንድ ሲሆን፤ ክፍል ሁለቱን ከዚህ በታች ያገኙታል። (ክፍል ሁለቱ የማይታይዮ ከሆነ “ሙሉውን አስነብበኝ ...” የሚለውን ይጫኑ!)
ሙሉውን አስነብበኝ ...የኢትዮጵያውያን ፎረም በአውሮፓ፤ በኔዘርላንድ ደን ሐግ ከተማ ጁላይ 29 ቀን 2016 እ.ኤ.አ. ባዘጋጀው ኮንፈረንስ ላይ፤ ዩሱፍ ያሲን ያቀረቡት ጽሑፍ።