ገላነው ክራር (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.)

ተስፋዬ በሰሞኑ ጽሁፎቹ መነጋገሪያ ሆኗል። ጽሁፎቹን አነበብኩ። የተስፋዬን ጽሁፍ ሳያነብ የሚያልፍ ያለ አይመስለኝም። አሁን አሁን፣ በተለይም ካገር ከወጣ በኋላ የሚጽፋቸው አብዛኛዎቹ እውነትነት ቢኖርባቸውም፣ በርካታ ጉዳዮች ላይ በግልጽ መናገር ሳይችል እስካሁን አለ። በተረፈ ጽሁፎቹ በቋንቋ እየሰሉ የሄደ ፀሐፊነቱን ይመሰክራሉ። ተስፋዬ የአጻጻፍ ስሌቱ ውብ ነው። የግሌ ሃብቱ ነው።

 

 

(አጫጭር አረፍተነገሮችን መጠቀሙ ከበዓሉ ግርማ የተማረው የሚመስል ከመሆኑ በቀር [ይህን ራሱም ተናግሯል ልበል?])። እኔ ”እንደወረደ” ነው የምለው የተስፋዬን ጽሁፍ። ዘይት ሲፈስ አይተህ ታውቅ ከሆነ እንዲያ ነው። ይወርድለታል። የአጻጻፍ ስሌቱን እንደቀናሁበት አለሁ። በመቶዎች የሚቆጠሩ የተለያዩ ቁርጥራጭ ሃሳቦቹን እንዴት እንደሚያገናኛቸው (ይህ ሁሉ አድናቆቴ ”የጋዜጠኛው ማስታወሻ”ን እያሰብኩ ነው፣ ሁለተኛውን መጽሐፉን አላነበብኩም) ... የተለያዩ ቁርጥራጭ ታሪኮችን እያንሰላሰልኩ እንደሱ የመጻፍ ችልታ ቢኖረኝ፣ ስንት እና ስንት ታላላቅ ሃሳብ በውስጤ ያለኝ ይመስለኛል። ማንስ የሌለው አለ? ”እያንዳንዱ ሰው በልቡ ውስጥ አንድ የሚጻፍ ታሪክ አለው” ያለው በዓሉ ግርማ ነበር? ... ”የጋዜጠኛው ማስታወሻ”ን ባንድ ቀንና ሌት (24 ሰዓት) ጨርሸዋለሁ።

 

አንዱ የሰሞኑ ጽሁፉ (”የአለማየሁ እህት”) ሳሊምቢኒን ይጠቅሳል። የጳውሎስ ኞኞንም መጽሐፍ ከስሩ አስፍሯል - ከመጽሐፉ ርዕስና ገጽ ጋር። በታሪክ-ቀመስ የፈጠራ ስራ ውስጥ፣ ደራሲ የባለታሪኮቹን ደግም ሆነ ክፉ ስራ የሚያይበት ማዕዘን ትልቅ ሚና ይጫወታል። ታሪኩ እውነት ቢሆንም እንኳን (”እውነት አይደለም” ብለው እየሞገቱት ያሉ አሉ። እውነት አላቸው። ምክንያቱም በአንድ የታሪክ ጉዳይ ወይም በባለታሪክ ታሪክ ላይ በተለያዩ ፀሐፍት የተለያዩ ጽሁፎች ሊወጡ ይችላሉ። ታሪክ ደግሞ ለዚህ የተመቸ ይመስላል።) በተለይም ኢትዮጵያ እንዲህ ፈታኝ በሆነ አጣብቂኝ ውስጥ ባለችበት ወቅት፣ የአገሪቱን ግዛት እና ዳር ድንበር በማስከበር ረገድ አለማቀፍ እና ታላቅ ታሪክ ያላቸው መሪዎች ድክመት ላይ ማጠንጠኑ አልተመቸኝም። አለዚያ ግን መብቱ ነው። እልፍም ሲል ደራሲ ሲጽፍ እገሌን ”ይመቸዋል?”፣ ”አይመቸውም?” ብሎ አይደለም። ይጽፋል። በቃ። ... (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ