ምነው ዲያስፖራ!

ዳግማዊ ዳዊት This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

ትናንት ለኢህአዴግ - ሲሠራ የነበረውን - “ያን ባለጌ ወራዳ

አላዋቂ ማይም - አጎብዳጅ - ለጠላት ያደረ ክፉ ባንዳ

ትምህርት ቤት ያልረገጠ - ደፋር ማይም - የማያውቀን ዘላባጅ

ህሊናውን የሸጠ - የወራዶች ሁሉ ውራጅ”

ተማረ እንዲባል ለስሙ - በመለስ ቀጭን ትዕዛዝ

እንዲመች ሆኖ - እንዲሠራ - ለወያኔው አገዛዝ

ሲቭል ሰርቪስ ገብቶ

በሕግ ተመርቆ ወጥቶ

ለአግአዚ ጦር አለቃ - ሆኖ - በኅዳር ሰማይ የጥይት መብረቅ ያጮኸ

እናቶችን በለቅሶ - በደረታቸው ያስዳኸ

ታዬ አሉ ዘንድሮ - እዚህ ዲሲ - አሜሪካ ምድር ገብቶ

“ሀገር ከድቶ - ከመለስ ተጣልቶ።”

ውሎ ሳያድር - ከተቃዋሚዎች ጎራ

ሲቀላቀል ሲያወራ

“ያንን ጠብደል ማይም - ያ ደደብ ያልነውን” ሰው

ይጀመራል ክፍከፋው - ይቀጥላል ምስጋናው

እናም በቆዩት ቦታ - እሱን ከፍ እናደርግና

ሊቅ ያለ እሱ ማን አለ - ብለን እንለውና

ትግሉ በወያኔ - ተመልሶ ሲጠለፍ - እናያለን እንደገና።

ወያኔ በስልቱ - በሚያውቀው ጎዳና

ጠላት አስመስሎ ወዳጁን - ማከላችን ያስገባና

ትግላችንን ሲያኮላሸው - መመዘን አቃተንና

ትግል ትግል እንላለን - ይህም ትግል ተባለና!

ምነው ዲያስፖራ - ምነው ሚናችን ቅጡን አጣ

የወያኔ ደጋፊ ነን - ወይስ ተቃዋሚ ባለአንጣ?


ዳግማዊ ዳዊት

This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

ጥቅምት 2003 ዓ.ም.

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ