ክንፈሚካኤል ገረሱ
እንዳሳዩት እንደመሩት፣
ወደ ገፉት ወደ ነዱት።
ከቀኝ ግራ ምልስ ቅልስ፣
ቧ! ቧቧቧ! ... ቧቧ! ፍስስ።


እቁር ስብስብ ክትር፣
እንዳዘዙት ሲጠማዘዝ ሲሽከረከር።
ሲያዋክቡት ከፊት ኋላ፣
ተኖ ሲደርቅ ወይ ሲሞላ።
አያናጥር በመሰለው፣
የቦይ ውሃ ምን ክብር አለው።


ክንፈሚካኤል ገረሱ
11/02/1992 ዓ.ም.

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ