ወለላዬ ከስዊድን
Saudis torturing Ethiopiansያልታየን አሟሟት - ባንተ አይቼ
ሞትህን በቁሜ ሞቼ
ሲገድሉህ የተሰበረ ቅስሜ
እስካሁን አልጠገነም ሕመሜ
ሲገሉሽ ሞቼ ነው የከረምኩ
ከስቃይሽ እኔም አልተረፍኩ 


Ethiopians killed in Saudi Arabia

ይህንን የናንተን አበሳ
ልጽፈው ብዬ ብነሳ
ኀዘን ዘልቆ ከገባ - አጥንት ድረስ
ለካስ ቃላትም - የአንጀት አያደርስ
'እዬዬም ሲዳላ ነው' ይባላል
እንባም ስቃይ ሲከብደው - ለካስ ይደርቃል
ደርቆ ይቅር! - ድሮስ ምን ሊጠቅም እንባ?!
ቃላትም በኖ ይጥፋ! - ያሻው ቦታ ሄዶ ይግባ!
ሁለቱስ ምን አባታቸው ሊያደርጉልኝ?
ሞታችሁን ብረሳ ግን - ያቺ ቀናችሁ አትርሳኝ! 

ወለላዬ ከስዊድን This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. 
በሳዑዲ ዐረቢያ ያለምንም ጥፋታቸው ለተጨፈጨፉት ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ መታሰቢያ ይሁን! 

 

 

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ