ጌታቸው አበራ (ፒ.ዲ.ኤፍ.)
መልካም አዲስ ዓመት! - ጌታቸው አበራ Happy New Year by Getachew Abera

የታሪክ አምድ ነባራዊ፣ ምድረ-ህይወት ፍልስፍና፣

መውጣት መውረድ፣ የዓለም ሕግ፣ የተፈጥሮ ገጽ ሆነና፣

ጊዜ ክፉ፣ ጊዜ ደጉ ...፣ እጥፍ-ዘርጋ፣ ዘመም-ቀና ...፣

አንዴ ጽልመት ...፣ አንዴ ብርሃን ...፣ ባለታሪክ፣ ባለዝና፤

ስትወድቂ ...፣ ስትነሺ ...፣ በዘመናት ጉዞሽ ሂደት፣

ለዚህ ደረስሽ፤ እልልልል! ሁለት ሺ ሰባት ዓመት!

ባለፊደል፣ ባለቀመር ...፣ የባህል ጌጥ መናኸሪያ፣

የእምነት አውራ፣ የእግዚአብሔር ቤት፣ የቃል-ኪዳኑ ማደሪያ፤

በመለኮት ብፁዕ ጸጋ፣ ዙሪያ-ገባ የተከበብሽ፣

በፈጣሪ ጥበቃ ስር፣ በኃያል ክንዱ የተደገፍሽ፤

‘አበቅቴ ውሉን ቢስት’፣ የዘመመ ቢመስል ቀኑ፣

እርኩስ መንፈስ ቢጣባሽም፣ ቢያስጨንቅሽ ሰቀቀኑ፣

ያምላክሽ ኃይል፣ ብርቱ ክንዱ፣ በልጆችሽ መንፈስ አድሮ፣

እማይቀር ነው ትንሣኤሽ፣ አዲስ ዘመን ዓመት ቆጥሮ፤

እስከዚያው ግን ይመስገነው፣ ትንፋሽሽም በመኖሩ፣

መልካም ዓመት! ለቅን ሕዝብሽ! ለውብ ገላሽ፣ ላገር-ምድሩ!

... (ሙሉውን ግጥም በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ይጫኑ!)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ