የፍቅር፡ የተስፋ እ'መቤት

የነጻነት ምንጭ፤ የደም ውጤት፡

ሰው የመሆን መለኪያ፡

የውበት ጥግ አምሳያ፡

የነጻነት ምልክት፡ መለያ፤

የማንነት መከታ ውቅር፡

የታሪክ ምሰሶ ማገር፤

ትከበሪያለሽ ሁሌም፡

ትዘከሪያለሽ በአለም፡

የድል ውጤት ነሽና፡

ትታወሻለሽ እንደገና፤

ደምቆ ያብባል ስምሽ፡

ህብር ድምቅ ነው ዝናሽ

አድዋ!

ክብርሽ ይታወስ ዛሬም

ይቀጥል... ነገና ከዚያም...

ደግሞም

እስከ ዘለ አለም ... አለም፡፡

ሲጠናቀቅ ፌብሪዋሪ 26/2015 ምሽት ነበር

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ