አለ አንድ ነገር (እሸቱ ታደሰ)
እሸቱ ታደሰ
በሆነ ባልሆነው ሕዝብን ከነካኩት
እሺ ይሁን ብሎ ችሎ ተሸክሞት
ይኖር ይኖርና ጊዜ እስኪመጣለት
አንድ ቀን ሲበቃው እምቢኝ ያለ ለታ
ግፉ ከጫፍ ደርሶ ሲበዛ ኡኡታ
ማንም አያቆመው እኔ ነኝ ያለ ወንድ
ያንቀጠቅጠዋል የትም ሸሽቶ ቢሄድ
ይኸው ተጀምሯል ባንድነት ትብብር
ቀኑ ተለውጧል አለ አንድ ነገር
ወኔ መች ጠፋና ከአምቦና ከጎንደር።
እሸቱ ታደሰ (Eshe Man Tade)