ክንፈሚካኤል ገረሱ

የትላንት አብሮ አደጉ ባልደረባው፣

የትላንት ወዳጁ ባልንጀራው፣

ስኬት ሲሸሸው ስኬት ሲርቀው።

ጥሎ ሲያሄደው ሲያደቀው ውድቀት፣

አዕምሮው ሲዝል ነፍሱ ስትቃትት።

ይሄኔ ነው የሰው ተንኮሉ የሰው ክፋቱ፣

ባልንጀራውን ማብጠልጠሉ ማጠልሸቱ፣

በእድገት በስኬት ሳይሆን በውድቀት መርካቱ፣

የሰው ክፋቱ።


ታህሳሥ ፴ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም.
ክንፈሚካኤል ገረሱ

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ