ዘ-ጌርሳም

አረመኔ ባይሆን ሰው ክፉና ጨካኝ

እመኝለት ነበር አንድ ሺህ ዓመት ቢያገኝ

አንድ ሞት አይደለም ብዙ ሞትን ይሙት

አዛኝ ልብ እርቆት ስለሌለው አንጀት

በልቶ ካልጠገበ

አይቶ ካልጠገበ

ሰርቆ ካልጠገበ

ዘርፎም ካልጠገበ

ለተገኘው ሁሉ ከተስገበገበ

ለምን ሞት ያንሰዋል የማይቀረው ነገር

በተሻለው እንጅ ሳይፈጠር ቢቀር

እንስሳ እንኳን በአቅሙ ተካፍሎ ይበላል

እንዴት ከዚህ ወርዶ ሰው መባል ይቻላል

ቃልኪዳን አፍርሶ

ማተቡን በጥሶ

በሰው ከመጠራት

ቢሰየም በአራዊት

ካላቸው ሕግጋት

በዚያው ለመዳኘት

የሰው ግብዝነት

ነግ በኔ አለማለት

አልሞ መድረሻን

በመርሳት መነሻን

በትዕቢት መሸፈን ዞር ብሎ አለማየት

ለሚዘረግፈው ጊዜው የመጣ ዕለት

አንገትን በመድፋት በውርደት በቅሌት

ለሰው ሞት አነሰው ከዚህ በላይ ቢኖር

ለፈጸመው በደል በከፈለ ነበር

አረመኔ ባይሆን ሰው ክፉና ጨካኝ

እመኝለት ነበር አንድ ሺህ ዓመት ቢያገኝ

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!