የረቡዕ ግጥም ፬ኛ ዓመት፣ ቁ. ፱

ግፍ አትሥራ
ሌላ ግፍ አትሥራ
የሰው ልጅ ተፈጥሮ፣ ጠቅላላ ባሕርይ፣ ስለሚወራረስ፣ አንዱ ከአንዱ ጋራ
በደልን ለማጥፋት፣ ግፍን ለማስቀረት፣ አንተም በዛው መንገድ ሌላ ግፍ አትሥራ።
ሰው መኾን መርሳት ነው፣ ተፈጥሮን መዘንጋት፣ አመልን ማዳፈን
ክፋትን ተንኮልን፣ ሴራ መጎንጎን፣ አንተ እንደማታውቀው እንዴሌለህ መኾን
ወለላዬ ከስዊድን (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.)