እንኳን አደረስዎ!
ወለላዬ ከስዊድን
ሆሳዕና
ማቴዮስ .21፥1-17
ወደ እየሩሳሌም ወደ ቤተፋጌ
ደርሰው ነበርና ደብረዘይት ግርጌ
በዛን ጊዜ ጌታ ደቀ መዛሙርቱን
እንዲህ ብሎ አዘዘ ጠራና ሁለቱን
ከዛ ከፊታችሁ ከምትገኝ መንደር
አህያ ታስራለች ከውርጫዋ ጋር
ሙሉውን አስነብበኝ ...ትዳርና ስደት
ወለላዬ ከስዊድን
በሕዝብ ተጋርደን ባ'ገር ተከልለን
ለካስ እኔና አንቺ ብዙም ዕውቀት የለን።
እኔን ስመረምር አንቺን እዚህ ሳይሽ
እኔም ያን አይደለሁ፤ አንቺም ያቺ አይደለሽ።
እንዲህ ካደረገን ስደት አሸንፎ
ጭራሽ ከሚለየን ኑሮሯችንን ገፎ
ሠርግ ባንደግስም ባይረጭ አበባ
በአዲስ ትውውቅ ድጋሚ እንጋባ።
ወለላዬ ከስዊድን This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
ወለላዬ
ከሚለጥፍብህ ከአፉ እንደመጣ
ሚሻለውን መርጠህ ለራስህ ስም አውጣ
ሺ ጨዋ ብትሆን ሚልዮን ጥንቁቅ ሰው
ሰው በሰውነትህ የሚልህ ስላለው
በችሎታህ መጠን ኪሎህን መዝነህ
ጭማሪ መጠሪያ ስም ስጠው ለራስህ
የሚጠራህ ከጠፋ አንተ ባወጣኸው
በተግባር ታይና ለስምህ ስም ሁነው!
ወለላዬ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
ገዛኸኝ ድንቁ (ከጀርመን)
ሥዕል ከሥነ ጥበብ የፈጠራ ሥራዎች ሙያ ዘርፎች አንዱ ነው። በኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጥናትና ምርምር ማዕከል በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የካቲት 1993 ዓ᎐ም. ባሳተመው ጥልቅ የሥነ ቋንቋ ጥናት የአማርኛ መዝገበ ቃላት ላይ ስዕል ቀጥተኛ ትርጉሙን እንዲህ ሲል ይፈታዋል።