ጫፍና ጫፍ (አትክልት አሰፋ)

ሁለት ጫፍና ጫፍ ያልተገጣጠመ፣

አንደኛው ቀና ሲል፤ ሌላው ያዘመመ፤

አቅጣጫ ሲፈልግ ጫፉ ለመጋጠም፣

ይሄኛው ሲራወጥ ከዚያኛው ሊጣጣም፣

አንዱ በዚህ ሲዞር፤

                ያኛው ወዲያ ሲያከር፣

የሚያለዝብ ጠፍቶ፤

                በየፊናው ሲበር፤

ምኞታቸው ሳይሰምር፤

                       ፍላጎት ሳይረካ፣

ወዲያ ወዲህ ሲሉ ጫፍ ሳይነካካ፤

ይሄን ጫፍ ከዚያኛው ማጋጠም ቢችሉም፣

ሁሉም ቢዳክሩም መፍትሄ አላገኙም።

            ጥሞና ሳይሰፍን በመሀከላቸው፣

            ፍላጎት ብቻውን ሲነድ በሆዳቸው

         ሁለቱም አንድ ሆነው፤ ሃሳብም ሳይሞላ፣

         መክነው እንዳይቀሩ በሉ እንፍጠር መላ።

 

ፌብሪዋሪ 8/2014 ቫንኩቨር (በርናቢ)

ፀሐይ (ክንፈሚካኤል ገረሱ)

ክንፈሚካኤል ገረሱ
"ተቃጥሎ ሲያበቃ 'ሂሊየም-ሃይድሮጂን'፣
ሁሉ አመድ ሲሆን ስትቀር ርቃኗን።
ያኔ ታሪክ ሆነች ፀሐይ አከተመች ፣ "
ይላሉ ጠበብቱ የምድር ፈላስፎች።
ስሚኝማ ፀሐይ! ንገሪኝ እውነቱን፣
'ሚያስተነትኑት ምሁራኑ 'ሚሉን፣
ያንቺ ማንቀላፋት ምጽዓት ማለት ይሆን?

ጤናችን ይጠበቅ በሁላችን

ተፈራ ድንበሩ
የወጣችሁትን ተራሮች ጥላችሁ
የሮጣችሁትን ሜዳዎች ትታችሁ
አፈር ሳር ቅጠሉ እየናፈቃችሁ
በምኞት በተስፋ ቀን እንዲያልፍላችሁ
በረሀ አቋርጣችሁ የተሰደዳችሁ
ከዘመድ አዝማዱ በመለየታችሁ
ባይተዋርነቱ ናፍቆት ሳያንሳችሁ
በሰው አገር ደግሞ ኑሮ እንዳይከፋችሁ
ያገር ቤቱን እድፍ ከልብ አጥባችሁ
ንጹሕን ልበሱ እናንተም ታጥባችሁ
ተባይ ተከትሎ ጤና እንዳይነሣችሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ