የረቡዕ ግጥም ፫ኛ ዓመት፣ ቁ. ፴፯
መብለጥህን ደብቅ
እንዳትቀየመኝ ጥፋተኛ አንተ ነህ
ሁሉ ቦታ ከኔ ማን ብለጠኝ አለህ?
አሁንም እባክህ መብለጥህን ደብቅ
አንተም አትጠላ እኔም አልሳቀቅ
ሙሉውን አስነብበኝ ...
እንዳትቀየመኝ ጥፋተኛ አንተ ነህ
ሁሉ ቦታ ከኔ ማን ብለጠኝ አለህ?
አሁንም እባክህ መብለጥህን ደብቅ
አንተም አትጠላ እኔም አልሳቀቅ
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ብተወኝ ምንአለ?
ዝቅ ካላለብህ ኑሮህ ካልጎደለ
እኔን እንዳመሌ ብተወኝ ምንአለ
አልጨምር አልቀንስ ፍጹም ካንተ ሕይወት
መኖሬ ምንድነው የሆነብህ ፍርሃት
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ወለላዬ (ማትያስ ከተማ)
በዱላ መቀጣቀጥ ብትችልም
መደባደብ፣ ማባረር፣ መግደልም
መፍትሔ ሆኖ ላያኖርህ ላያቆይህ
ጥፋት ነው ለጥፋት ማቆብቆብህ
በጣጥሰህ ሸንሽነህ ካልከፋፈልካት
ሰላም አውለህ ሰላም ካሳደርካት
አገርህ እንደኹ ለሁልኽም በቂህ ናት
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ይወረወር ነበር
ሻማ ጉራ ብቻ፤ ቁመታም ቀፈረር
ቆሞ እያለቀሰ ሲያነባ የሚኖር
ክር መኻል ሆና እውስጡ ባትነድ
ይወረወር ነበር እንደ ድንጋይ መንገድ
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ከቤትም አንወጣ
አእምሮም ያስባል
ኩላሊት ያጣራል
ልብም ደም ይረጫል
ጨጓራም ይፈጫል
ከሁሉም ከሁሉም - ማን እንደፊንጢጣ
እፎይ ባያሰኘን - ከቤትም አንወጣ
ሙሉውን አስነብበኝ ...