የረቡዕ ግጥም ፫ኛ ዓመት፣ ቁ. ፵፩

ጓደኞቹን ቁጠር
ሐሜት አቀርሽቶት ፊትህ ሲዝረበረብ
እሱን እዛው ትተህ አስቀምጠህ በገደብ
ምን ያህል እንደሆን ያቦካው ሰው ድምር
ለማወቅ ከፈለክ ጓደኞቹን ቁጠር።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ሐሜት አቀርሽቶት ፊትህ ሲዝረበረብ
እሱን እዛው ትተህ አስቀምጠህ በገደብ
ምን ያህል እንደሆን ያቦካው ሰው ድምር
ለማወቅ ከፈለክ ጓደኞቹን ቁጠር።
ሙሉውን አስነብበኝ ...አለመተማመን በልባችን ይዘን
እንድንተማመን ሰው አቁመን ማልን
መሃላ ስናፈርስ ሰዉ ዝም ሲለን
በጥፋት ፈራጁን እግዜርን ረሳን
ሙሉውን አስነብበኝ ...እንግድነት መጥቶ፣ “ቤት የእግዜር!” ብንለው
“ገብረ”ን ጨመረና የራሱ አደረገው
አፋችንን ይዘን ገርሞን ስንሳሳቅ
ከቤት አስወጥቶን ሠራበት ትልቅ ፎቅ
ሙሉውን አስነብበኝ ...አልችልም ላወጋው ልናገር ጨርሶ
የዘመኔን ኀዘን የዘመኔን ለቅሶ
ዓይኔም ታዘብኩት ጆሮዬም ገረመኝ
ስንቱን ጉድ አየሁት ስንቱን ጉድ አሰማኝ
ሙሉውን አስነብበኝ ...በበረዶ ሰልፍ ወጥቼ፣ ጠላትን በአደባባይ አውግዤ
አገር ነፃ ወጥታ፣ እኔም ነፃ ልወጣ፣ እፎይ ልል ተስፋ አርግዤ
ባንዲራዋን ተጠቅልዬ፣ ከፍ አድርጌ ተሸክሜ
ገጿ ባክኖ ቢርቀኝም፣ የሷን ምስል ልቤ አትሜ
በየመንገዱ ግርጌ፣ በየቢሮው ደጃፍ ድኼ
ቀን ለፈረንጅ ጆሮ፣ ማታ ለጭንቅ አማልጇ ጮኼ
ሙሉውን አስነብበኝ ...