እውነት አንተም ኢትዮጵያዊ ነህ?! (ወለላዬ)

Shashemene

ወለላዬ ከስዊድን

“አዎን! ኢትዮጵያዊ ነኝ!” በለኝ

መቼም አፍህ ከተግባርህ አይከብደኝም

ካልኾንክም ግድ የለም

እቅጩን ሐቁን ንገረኝ

ያንተ ነገር ቁርጡ ይግባኝ።

የኔነቴን የአገሬን ትዝታ

የቀዬው የአድባሩን ሽታ

የፍቅሬን የአንድነት ጥላ

ለዘመናት ያኖረኝን ከለላ

ወዲያ ጥለኸው ሰባብረህ

ከናት ካባትህ ቃል ኪዳን ርቀህ

እንዲህ ኾነህ ያገኘሁህ

ማነህ?

እውነት አንተም ኢትዮጵያዊ ነህ?!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ይብላኝ ወንድሜ፣ ላንተ ይብላኝ! (ወለላዬ ከስዊድን)

PM Dr. Abiy Ahmed

ወለላዬ ከስዊድን

ስንቱን ጉድ ይኾን የምታልፈው? ስንቱ ጉድ ይኾን የሚያልፍህ?

ለተነሳህበት ዓላማ፣ ለአንድነት፣ ለመደመር፣ ለብልጽግና የሰላም ጉዞህ።

ስንት ውትብትብ ይኾን የምትፈታው

ተናግረህ ምታሳምን - ተሻግረህ ምታሻግረው

እየሠራህ ላለኸው ላንተ ይቅርና ለእኔ ደከመኝ ያንተ ጣር፣

እንዴት ይኾን? የአንድ ቀን ውሎህ? እንዴት ይኾን? የአንድ ቀንህ አዳር

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ደግሞ ደፈረሰ ሰልፍ ልውጣ! (ወለላዬ)

ሰልፍ

በበረዶ ሰልፍ ወጥቼ፣ ጠላትን በአደባባይ አውግዤ

አገር ነፃ ወጥታ፣ እኔም ነፃ ልወጣ፣ እፎይ ልል ተስፋ አርግዤ

ባንዲራዋን ተጠቅልዬ፣ ከፍ አድርጌ ተሸክሜ

ገጿ ባክኖ ቢርቀኝም፣ የሷን ምስል ልቤ አትሜ

በየመንገዱ ግርጌ፣ በየቢሮው ደጃፍ ድኼ

ቀን ለፈረንጅ ጆሮ፣ ማታ ለጭንቅ አማልጇ ጮኼ

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ተገዳድለህ መፍትሔ አታመጣም!

Stop killing each other!

ወለላዬ (ማትያስ ከተማ)

በዱላ መቀጣቀጥ ብትችልም

መደባደብ፣ ማባረር፣ መግደልም

መፍትሔ ሆኖ ላያኖርህ ላያቆይህ

ጥፋት ነው ለጥፋት ማቆብቆብህ

በጣጥሰህ ሸንሽነህ ካልከፋፈልካት

ሰላም አውለህ ሰላም ካሳደርካት

አገርህ እንደኹ ለሁልኽም በቂህ ናት 

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ለባለ ተረኞቹ

ከመኮንን ልጅ

27 ዓመታት ሲታገል የኖረው
ሲታሰር ሲገደል ሲሰደድ የከረመው
በወያኔውም በአሽከሩም ሲታምስ ሲታመስ
ትግሉን አርግዞ ምጡ ላይ ሲደርስ

ከወያኔው ሰፈር ካሽከሮቹ መንደር
ትግሉ ጫፍ መድረሱን እጅግ በመጠርጠር
ከሉሌነት ይልቅ ሰው መሆን የመረጡ
ሲመሽ ተቀላቀልው መሪ ኹነው መጡ

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በተመኘሁለት (ዘ-ጌርሳም)

ዘ-ጌርሳም

አረመኔ ባይሆን ሰው ክፉና ጨካኝ

እመኝለት ነበር አንድ ሺህ ዓመት ቢያገኝ

አንድ ሞት አይደለም ብዙ ሞትን ይሙት

አዛኝ ልብ እርቆት ስለሌለው አንጀት

በልቶ ካልጠገበ

አይቶ ካልጠገበ

ሰርቆ ካልጠገበ

ዘርፎም ካልጠገበ

ለተገኘው ሁሉ ከተስገበገበ

ሙሉውን አስነብበኝ ...

መስሎህ ነበር (ዘጌርሳም)

ዘጌርሳም

የረጅም ጊዜ ተንኮላቸው ሳይገባህ

አጀንዳቸውን ሳታነብ ሳይረዳህ

በቋንቋና በባህል አሳበው

መገንጠል አለብህ ብለው አታለው

አንድ ‘ርምጃ ወደፊት አራት ‘ርምጃ ወደኋላ ስበው

የልጆችህን ዕድል አጨልመው

ያንተንም ሕይወት አደንቁረው

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የመደመር ቋንቋ (ሶምራን)

ሶምራን

በመደመር ቋንቋ በፍቅር ዜማ ውሰጥ፤

ያለችውን ቅኝት አገር ሰታስነሳ መሬቱ ሲቀውጥ።

እኔ ነኝ ብቻ የሚል ከበሮ ቢመታ ነጋሪት ቢደለቅ፤

ሰሚ ጆሮ አይኖርም ቋንቋውም አይታወቅ።

ሁለት ዘር ኖሮኝ በየቱ ልከበር በየትኛው ልናቅ፤

መደመር ባይታለም መደመር ባይታወቅ

እንደምን ይቻላል ቢባል ከአካልህ መሐል አንዱ ክፍልህ ይጣል አንዱ ክፍልህ ይውደቅ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ