Nelson Mandelaፍቅር ለይኩን (ከደቡብ አፍሪካ)

የነፃነት አርበኛ፣ የይቅርታ አባት፣ የፍቀር ተምሳሌት፣ የአይበገሬነትና የፅኑ መንፈሥ ባለቤት፣ የመለያየትንና የዘረኝነትን ፅኑ ግንብ በማይለወጥ ፍቅር ያፈረሱ፣ የሠላም መልዕክተኛ፣ የሰው ልጆች ሁሉ የአንድነት ምልክት፣ ... ወዘተ በሚሉ ቅጥያ ስሞች በሚታወቁት በዛሬው የ92 ዓመት አዛውንት ኔልሰን ማንዴላ የትግልና የፖለቲካ ሕይወት ውስጥ ሀገራችን ኢትዮጵያ ያላት ሥፍራ በእጅጉ የተለየ ነው።

 

የእናት ምድራችን የረዥም ዘመን የነፃነት ታሪክ በአንድ ወቅት በዚሁ በደቡብ አፍሪካውያን መራራ የነፃነት የትግል ታሪክ ውስጥ በጉልህ የሚወሳ ለጥቁር ህዝቦች የኢትዮጵያ አንፀባራቂ የነፃነት ታሪክ የሚራልና የወኔ ስንቅ ሆኗቸው እንደ መርግ የከበደ የአፓርታይድን የዘረኝነት አገዛዝ ከጫንቃቸው ለመጣል የዛሬይቱ ተመፅዋች ድሃ የረሃብና የጦርነት ምድር ተብላ የምትጠራው ምስኪኗ ኢትዮጵያ በትላንቱ ረዥም የጥቁር ህዝብ እልህ አስጨራሽ የፀረ-ቅኝ ግዛትና የፀረ ባርነት ትግል ውስጥ ትልቅ ተምሳሌት ነበረች። ... (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ