እስክንድር ነጋ

የደርባባውና የ82 ዓመቱ አዛውንት ሆስኒ ሙባረክ ከስልጣን መውረድ ዓርብ አመሻሽ ላይ ሲበሰር፣ በግብፅ ታሪክ ተሰምቶ የማይታወቅ እልልታና ሆታ ቀለጠ... ሕዝብ በደስታ ሰክሮ ሌሊቱን አሳለፈ.... አይ ካይሮ ያቺን ምሽት!... እንዴት ትረሳለች?... እኛስ አብረናቸው አላደርንም እንዴ?... ዕድሜ ለአልጀዚራ፣ ለቢ.ቢ.ሲ፣ ለሲ.ኤን.ኤን፣ ለፕሬስ ቲቪ... የካይሮ ሕፃናት እንዴት ይረሱናል?... ገብቷቸው ይሆን እንዲያ የፈነጠዙት?... ጨለማውን ብርሃን እንደዋጠው እውን ለእነሱም ታይቷቸው ነበርን?... ቀልባቸው ነግሯቸው ይሆን?... የትላልቆቹማ ምኑ ይወራል... በእነሱ ደስታ እኛም እምባ ተራጭተናል ...

ቆም ብሎ ለማሰብ አፍታ የተገኘው በነጋታው ነበር፤ ዕለተ ቅዳሜ። ለመሆኑ፣ አዲሶቹ የግብፅ መሪዎች ከቶ እነማን ይሁኑ? የሕዝቡን የዲሞክራሲ ተስፋ አክብረው ተግባራዊ ማድረግ የሚችሉስ ናቸውን? መቼስ፣ ብዙ ሚሊዮን ሕዝብ ወጥ መልስ ይኖረዋል ተብሎ አይጠበቅም። ያ እንደ አንድ ቤተሰብ ተመሳጥሮ ሙባረክን ያንበረከከ ሕዝብ ግን፣ የቅዳሜ ጀምበር ገና ሳትጠልቅ ስሜቱ ተደበላልቆ አረፈው። የሚያስገርም ፍጥነት። ይባስ ብሎ፣ የሕዝባዊው ተቃውሞ እምብርት በነበረችው ታሂር አደባባይ ጎራ ለይቶ በመፈክር መፋለም ጀመረ። ... (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ