በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ… (የግል አስተያየት - በአያልሰው ደሴ)
’በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ’፣ በዙሪያ ጥምጥም ችግሮች ላይ ”የሕገ-መንግሥት” ቀውስ ሲታከል
የዜጎችን አንድነትና እንደ-ሕዝብ በጋራ መቆምን የግድ የሚል ዳግም የፈተና ጊዜ
አያል ሰው ደሴ (የግል አስተያየት) ሐምሌ ፲ ቀን ፪ ሺህ ፬ ዓ.ም.
(ከሁሉ በፊት የዚህ አጭር ጽሑፍ ዓላማ መነሻው የአቶ መለስ ዜናዊን የጤንነት ሁኔታ የተመረኮዘ ይሁን እንጂ ስለጤንነታቸው ይዞታም ሆነ እሳቸው ላይ ያተኮረ እንዳልሆነ ይታወቅልኝ።) የህወሓቱ የዕድሜ-ልክ መሪና ላለፉት ሃያ-አንድ ዓመታት በኢትዮጵያ አገራዊ ሥልጣን ቁንጮ ሆነው የቆዩት አቶ መለስ ዜናዊ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለሕይወታቸው ያሰጋ ከፍተኛ የጤና መታወክ የደረሰባቸው የመሆኑ ዜና ከተሰማ ጀምሮ የኅብረተሰባችን ዋነኛ የመወያያ ርዕስ እንደሆነ ይታወቃል።
የአቶ መለስን የጤና ሁኔታ ከራሳቸው፣ ከፈጣሪያቸውን ከቅርብ ሐኪሞቻቸው ውጭ በትክክል የሚያውቅ ያለ አይመስለኝም። የጤንነታቸው ሁኔታ በሕይወት ካለመኖር እስከ አገግሞ ድንገት ብቅ እስከማለት ሊያደርስ መቻሉ፤ ወይንም በሕይወት ኖረውም በሥራ ገበታቸው ላይ ለመሰለፍና እስካኑን ተቀናቃኝ በሌለው መልክ ይዘውት የቆዩትን ሙሉ የሥልጣን ኃላፊነት መወጣት የማይችሉ ”የቁም-ሙት” ሊያደርጋቸው ይችልም እንደሆነ በበኩሌ አላውቅም። የጤናቸው ሁኔታ ምንም ይሁን ምን ግን የገጠማቸውን የጤና መታወክ ተከትሎ ዜጎችን የምር የሚያሳስቡ ጥያቄዎች መነሳታቸው የግድ ሆኗል። ... (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)



