ዲያስፖራ ላሜ ቦራ (ወንድሙ መኰንን፣ ከታላቋ ብሪታኒያ)
ወንድሙ መኰንን - ከታላቋ ብሪታኒያ
ከኢትዮጵያ የሚደርሱን ቀልዶች ለዛቸው ጨምሯል። ሰሞኑን፣ አንድ ከአገር ቤት የመጣ እንግዳ፣ የወያኔ ባለሥልጣናት፣ ዲያስፖራን “ላሜቦራ” እያሉ እንደሚሾፉብን አጫውቶን አዝናንቶናል። እውን እኛ በተለያዩ ምክንያቶች ከኢትዮጵያ የተሰደድን ኢትዮጵያውያን ያለማቋረጥ የምንታለብ የካሽ ጥገቶች ነን? መቼም በኔዕድሜ ትምህርት ቤት የሄዳችሁ ሁሉ፣ ስለላሜቦራ የተተረከ የልጆች ጣፋጭም አሳዛኝም ታሪክ ሳታነቡ ወይም ሳይነበብላችሁ አልቀረም። የላሜቦራ ታሪክ እጅግ አንጀት የሚበላ ተረት ነው። ነገሩእንዲህነው። አንዲት ሁለት ሕጻናት የነበሯት እናት በጣም አሟት በአልጋዋ ላይሁና ትጣጣራለች። እሷስትሞት ባሏ ሌላ ሚስት ካገባ፣ የእንጀራ እናት በልጆቿ ላይ ለታደርስ የምችለውን ጭካኔ ስትገምተው ከራሷ መሞት በላይ አስጨነቃት። ከዚህም የተነሳ፣ ሰው አላምን ብላ (ሰው ምን ይታመናል? ዛሬ እዚህ ብታስቀምጠው ነገ ሌላ ቦታ ተንሸራትቶ ታገኘዋለህ) የምትወዳትን ላሜቦራ የተባለችውን ላሟን አልጋዋ ድረስ አስመጣቻት። “ላሜቦራ! ላሜቦራ! የልጆቼን ነገር አደራ” ብላ አዜማ እንደጨረሰች ሞተች። ሟቿ እናት እንደ ገመተችውም፣ የልጆቹ አባት፣ ብዙም ሳይቆይ ሌላ ሚስት አገባ። እንጀራ እናቲቱ ሕጻናቱ የሷልጆች ባለመሆናቸው በጣም ጨከነችባቸው። በረሀብ መንምነው እንዲሞቱ፣ ምግብም ትከለክላቸው ገባች። ልጆቹ ሲርባቸው፣ በቀጥታ ወደ ላሚቱ እየሄዱ፣ “ላሜቦራ! ላሜቦራ! የእማምዬን አደራ” ብለው ሲያዜሙላት፣ ላሜ ቦራ እግሮቿን ፍረክረክ አድርጋ ከጦቶቿ በቀጥታ ወተት እንዲጠቡ ታደርግ ነበር። ቀሪው ታሪክ ገብስነው። የሚገርመው ነገር፣ ላሜ ቦራ ያለመንጥፏ ነው። ክረመቱንም በጋውንም ዓመቱን ሙሉ ብትታለብ፣ ብትታለብ የማትነጥፍ የወትት ጅረት ናትተ ብሎ ነው የሚገመተው! (ሙሉውን ጽሁፍ በፒ.ዲ.ኤፍ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ)