ኢያሱ ዓለማየሁ

የኢሕአፓ 41 ዓመት መራራና ረጅም ትግል ረጅም ትግስትን ጠይቋል። አያሌ ፈተናዎችን ተቋቁሞና አልፎ ዛሬም ህልውናውን ጠብቆ በትግሉ ሜዳ ላይ መገኘቱ በቅድሚያ የአባላቱታሪክን ገርተውና ጽፈዋት ያለፉትም ሆነ በሕይወት ያሉትን ጽናትና ቆራጥነትየሚመለከት ነው። ኢሕአፓን ለመመስረትና መስርቶም ለማታገል በተደረገው ትግል በታሪክ አጋጣሚ ዋና ተካፋይ ሆኜ በመቆየቴ የሚሰማኝ ደስታና ክብርም ወደር የለውም። ሀቁ ይህ ድርጅት ከቶም ባልተመሰረተ የሚሉት ጠላቶች እንደ ነበሩትና እንዳሉት ሁሉ (በአብዛኛው ከስርዓቶቹ ጋር የተያያዙ) ቤዛችን ነው፣ የወኔያችን መከሰቻ ነው፣ የሀገር አለኝታችን ነው ድርጅታችን ነው የሚሉ ደሞ ብዙዎች ናቸው።

 ስለ ተማሪው እንቅስቃሴም ሊተቹ የተነሱ ብዙዎች በእንቅስቃሴው ያልተሳተፉና ውስጡንም የማያውቁ መሆናቸው የታዘብነው ነው። መሬት ላራሹ ብለው ተለቆቻችን በተሰለፉ ቀጣይ ዓመት ወደ ዩኒቨርሲቲ የገባነው ሁሉ እነ ሃይሉ ገሞራውን፣ ብርሃነ መስቀልን ወዘተ ማድነቃችን የግድ ነበር።(ሙሉውን ጽሁፍ በፒ.ዲ.ኤፍ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ)

 

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ