ወያኔ - በብሔር ብሔረሰቦች መነገድ ይብቃህ!
ኢትዮጵያ የሁሉም እኩል ሀገር ትሆናለች
ደመቀ በሪሁን
በዓለም ላይ በየጊዜው በርካታ የታሪክ አጋጣሚዎች ይፈጠራሉ። አንዳንዶች የተፈጠረውን አጋጣሚ በሚገባ በመጠቀም ለአገርና ለህዝብ የሚጠቅም ታላላቅ ሥራዎችን ይሠራሉ፤ ሌሎች በአንፃሩ የተፈጠረውን አጋጣሚ በማባከን ሀገርንና ህዝብን የሚጎዳ ታሪካዊ በደል ይፈጽማሉ። ወያኔ በኢትዮጵአ በተፈጠረው አጋጣሚ ለመንግሥት ሥልጣን በቅተሃል፣ የተፈጠረውን አጋጣሚ ለምንና እንዴት እየተጠቀምክበት እንደሆነ መመልከት ጠቃሚ ነው።
የኢትዮጵያ ህዝብ በገዥዎች የደርስበት የነበረውን በደል ለማስወገድ አመጽና ትግል አካሂዷል። ሁሉም ትግሎች ብሶት የወለዳቸው እንደመሆናቸው በነፃነት፣ በዲሞክራሲና ፍትህ ጥያቄዎች ላይ አተኩረዋል። የወያኔም የብሶት ትግል በእነዚሁ ጥያቄዎች ላይ ያተኩራል የሚል ግምት ነበር።
በኢትዮጵያ ረጅም የመንግሥት ታሪክ ሥልጣን ይያዝ የነበረው በጦርነት ሲሆን፣ አቅምና ጉልበት የነበረው ሥልጣን ሲነጥቅ፣ ተሸናፊው ይወገዳል። የሁሉም ገዥዎች ዓላማ ግን የኢትዮጵያን አንድነት፣ ዳር ድንበርና ሉዓላዊነት ጠብቆና አስከብሮ መግዛት ነበር። ... (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ይጫኑ!)