ከሰሞኑ ጫጫታ ባሻገር፣ የትብብሩ መሠረቶችና ተግዳሮቶች በቅጡ መዳሰስ
ዩሱፍ ያሲን (ኦስሎ)
ከሰሞኑ ጫጫታ ባሻገር
የሞላ አስገዶም ኩብለላ፣ ፍርጠጣ ክሕደት ወይም በመንግሥት ደጋፊዎች እንደተባለው ወሽመጥ በጣሽ የጀግንነት ሥራ በአሥመራ ተጓዞችና ደርሶ - ተመላሾች መሓል እየተቋጠረ መጥቷል ብለን ያሰብነው ንትርኩን እንደገና አደበላለቀው።
ቀደም ብሎ በስምምነት ባይደመደምም ቅሉ እልባት እተበጀለት የመጣ ሲመስል የነበረው ትግል በአሥመራ በኩል ያዋጣል፣ አያዋጣም ባዮች መሓል በትግል ምርጫና በትግል ማንኮባኮቢያ መሬት፣ የአስተናጋጁ መንግሥት ቃልኪዳን ጠባቂነትና ቃል አባይነቱ ዙሪያ በተለያዩ የኢትዮጵያ ታቃዋሚ ኃይሎችና ጉዳዩ ይመለከተናል ባይ ግለሰቦች መሓል ጊዜ ያስቆጠረው ንትርክና እሰጣ አገባን እንደ አዲስ አቀጣጠለውና ሰሞነኛው የወይይት ርዕሰ ጉዳይ አድርጎት አረፈው - የሞላ ኩብለላ። ጥሬ አረገው ባይባልም ቅሉ እንደገና ትኩስ አረገው። ላለፉት ሦስት ሳምንታት እያንጫጫን የሚገኘው የሞላ ጉዳይ ነው። ... (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)