ወያኔ የኦሮሞ ጠላት ነው

አንተነህ መርዕድ

Abayi Tsehaye አባይ ፀሐዬ

መለስ ሲያጉረመርምበት ብርክ የሚይዘውና የሚሙለጨለጨው፣ ጓደኞቹን ደጋግሞ በፍርሃቱ የሸጠው አባይ ፀሃዬ ዞር ዞር ብሎ ሲመለከት ከሱ የተሻሉና የሚያስፈሩት ህወሃቶች የሌሉ መሆናቸውን በማረጋገጡ በየመድረኩ ብቅ እያለ መፎከርና መዘባረቅ የእለት ተእለት ሥራው ሆኗል። በተለይም በዋና ባለቤትነት የአዲስ አበባን መሬት ሸጦ ከጨረሰ በኋላ የአካባቢውን ገበሬዎች ከነመሬታቸው ሊቀራመት ያደባበት ተንኮል አልሠራ ሲል “ልክ እናስገባቸዋለን” ሲል ፎከረ። አሁን ደግሞ ፉከራው የለኮሰውን እሳት ማዳፈን ተስኖት “ወያኔ የኦሮሞ ጠላት አይደለም” የሚል የሽሽት ሽምጥ ሩጫ ይዟል። እሳቱ ግን እሱን ሳይለበልበው የሚመለስ አይደለም።

ወያኔ ወደ ምኒልክ ቤተመንግሥት ሲገሰግስ ኦነግን ከተኛበት ቀስቅሶ ያመጣው ለኦሮሞ ህዝብ ጥቅም ብሎ ሳይሆን በኦነግ እጅ ኦሮሞውንና ሌሎችንም ለመሸንቆጥ ወይም ልክ አስገብቶ ለመግዛት መሆኑን ለማወቅ ቀናት አልወሰደም። ወያኔዎች እንኳን ለኦሮሞው፣ ቆመንለታል ላሉት የትግራይ ህዝም ቢሆን ገና ከመጀመርያው ጠላቱ እንደሆኑ ድርጊታቸው መስክሯል። ህወሃት ጠፍጥፎ የሠራውን ኦህዴድን ማንም ስለማያውቅና ስለማይቀበለው ኦነግን ለመሸጋገርያነት ማዘጋጀታቸውን የማያውቁት የጊዜው የኦነግ አመራሮች ብቻ ነበሩ። ኦነግ ሳይሆን በስሩ የተሰባሰበው ህዝብ የወያኔን ተንኮል ቀድሞ በመረዳቱ አልገዛም ሲላቸው ወያኔዎች ሰይፋቸውን የመዘዙት በጓደኞቻቸው የኦነግ አመራሮች ሳይሆን በኦሮሞ ህዝብ ላይ ነው። አመራሮቹን ቀስ አድርገው ከአገር ከመሸኘታቸው በፊት “ሰራዊታችሁን ካምፕ ውስጥ አስገቡልን” አሏቸው።

በአሜሪካና በሻዕብያ ዋስትና ሰጭነት ሰራዊቱን ከህዝቡ መሃል አስወጥተው ካምፕ አስገቡላቸው። የሚገርመው የተመረጡት ካምፖች ከወያኔ ሰራዊት በቅርብ እርቀት ላይ ተወስነው በቀላሉ የሚደርስባቸው እንዲሆኑ የተመቻቹ መሆናቸው ነው። በጊዜው ኦነግን ወክሎ ምርጫ ለማስፈፀም ደሴ ተመድቦ ከነበረው የኦነግ አመራር አባል ከሆነው ነገሪ ፈይሳ ጋር ለመገናኘትና ለመግባባት እድል አግኝቼ ነበርና ካምፕ ማስገባቱም ሆነ የተመረጡት ቦታዎችን አደገኝነት፣ ሻዕብያና አሜሪካ ከኦነግ ይልቅ ወያኔን የኋላ ኋላ እንደሚደግፉ ሃስቤን ስሰነዝርለት የሁኔታውን አሳሳቢነት የተረዳ አልነበረም። ጉዳዩ እንግዳ ቢሆንበትም ኋላ ላይ በከፋ ሁኔታም ቢሆን ሳይማር አይቀርም። የሆነውም ይሄው ነው። ወዳጄ ነገሪ ፈይሳና እነ ሌንጮም ሰራዊቱን አስረው አስረክበው እነሱ በቦሌ የመውጣት የቪዛ ሽልማት አገኙ። የገረመኝና እስከ አጥንቴ የሰበቀኝ ነገር፤ ያለምንም ፋታ ኦሮሞዎችን በመጨፍጨፍና በማሰቃዬት የተካነውን መለስ ዜናዊን እስትንፋሱ በሞት እስክታቆም ድረስ ሲገናኙት መኖራቸውን ሌንጮ ለታ ሲናገሩ የሰማሁ እለት ነው። በምን ተስፋ? በምን ውለታ? አቶ ሌንጮ!

በወቅቱ የወያኔን ሰራዊት የሚመራው የመከላከያ ሚኒስትሩ ስዬ አብርሃ በካምፑ ውስጥ ያሉትን በመክበብ የሚገድለውን ገድሎ የተረፈውን እስር ቤት ውስጥ ሞላቸው። እስር ቤቶች ኦሮምኛ መናገር የጀመሩት ስዬ ከጓደኞቹ ተጣልቶ እስር ቤት በገባበት ወርቅት ሳይሆን እሱና ጓደኞቹ የኦሮሞን ልጆች እንደ አውሬ እያደኑ በገደሉና ባሰሩ ጊዜ ነበር። “የአይጥ ምስክሯ ዲንቢጥ” እንዲሉ “እስር ቤቶች ኦሮምኛ ይናገራሉ አለ ስዬ” እየተባለ ሲጠቀስ ይገርመኛል። እውነቱ እውነት ቢሆንም የድርጊቱ ፈፃሚዎችን ምስክርነት ግን የሚጠይቅ አይደለም። ወያኔ ገና ጫካ እያለ ያቀደውን ነው ተግባራዊ ያደረገው። ስዬ፣ ገብሩ፣ አዳነች ወዘተ እጃቸውን እንደጲላጦስ እየታጠቡ ከደሙ ንጹህ ለመሆናቸው ብዙ ሊሉን ይችላሉ። በድርጊታቸው እንጂ በአፋቸው የማይነግሩን እውነት ቢኖር ኢትዮጵያንና ህዝቧን የሚጠሉ መሆናቸውን ነው። በአባይ ፀሃዬና አሁን ባሉትም ሆነ በተገለሉት የህወሃት መስራቾች መካከል ምንም ልዩነት የለም ። ቢኖርማ አሁን በኦሮሞ፣ በጋምቤላው፣ በአማራው፣ በአጠቃላይ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚሠራውን ግፍ ዝም ብለው አይመለከቱም ነበር። የትግራይ ህዝብ ተነካ ብለው አይደለም እንዴ መሳርያ ይዘው ጫካ የገቡት። ዛሬ ምነው አደባባይ ወጥተው አገር ልትፈራርስ ስትል ያልጮሁ?

ወያኔ የኦሮሞ ጠላት አለመሆኑን ከዚህ በታች ያለውን ሰንጠረዥ ተመልከቱና ፍረዱ። እስር ቤቶች በኦሮሞ የተሞሉ ብቻ ሳይሆኑ የግፉ ሁሉ መጨረሻ ዝግናኝ ኢሰብአዊ ድርጊት ሁሉ የሚፈጸምባቸው ቦታዎች ናቸው። ዝርዝሩን ለኦሮሞዎች የሚቆረቆር አካል ለቅሞ ያወጣው ቢሆንም እውነቱን አጉልቶ ያሳያልና በጥሞና ተመልከቱት። ከአምስት መቶ በላይ የሆኑ እስረኞችን ዝርዝር የያዘ ቢሆንም ሞትና የእድሜ ልክ እስራት የተፈረደባቸውን ሰማንያ ሰዎች ብቻ መርጨ ነው ያቀረብሁት። ከዚህ ዝርዝር በተጨማሪ ከየመን ተጠልፎ እስር ላይ የሚገኘውንና የሞት ፍርድ የተፈረደበትን አንዳርጋቸው ጽጌን አትርሱ። በዚህም አያበቃም፤ ባይታሰሩም ብርሃኑ ነጋ፣ አበበ ገላው …..እያላችሁ በወያኔ እጅ ባይኖሩም እድሜልክና ሞት የተፈረደባቸውን ኢትዮጵያውያን በህሊናችሁ እያሰባችሁ ዝርዝሩን ማስፋት ትችላላችሁ። እነዚህ ሁሉ ኢትዮጵያውያን የትኛው ወንጀላቸው ነው ሞትና እድሜልክ የሚያስፈርድባቸው? ላለፉት ሃያ አምስት ዓመታት በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን የገደሉና እየገደሉ ያሉ ህወሃቶች ምን ሊፈረድባቸው ነው? ነፃውን ፍርድቤትም በህሊናችሁ ነፃነቱን ቃኙት።

እውነቱን ባይቀይረውም በዝርዝሩ ላይ ስህተት ካለ እታረማለሁ።

ተ.ቁ

የእስረኛው ስም ፆታ ብሄር የተወነጀለበት ጉዳይ  ፍርድ እስር ቤት
1 አበረ አሰፋ አበራ ወንድ አማራ ሽብር ሞት ቃልቲ
2 አህመድ እስማኤል ሙዳሙመድ ወንድ ኦሮሞ ሽብርና ለጦርነት ማነሳሳት ሞት ቃልቲ
3 በያን አህመድ እስማኤል ወንድ ኦሮሞ ሽብርና ለጦርነት ማነሳሳት ሞት ቃልቲ
4 ዲሪቢ ኢታናገመቹ ሴት ኦሮሞ ሉአላዊነትን በመፃረር ሞት ቃልቲ
5 ኢብራሂም ሃሰን ናሊያ ወንድ ኦሮሞ ሽብር ሞት ቃልቲ
6 ጀማል ሙስጠፋ አደም ወንድ ኦሮሞ ሽብርና ለጦርነት ማነሳሳት ሞት ቃልቲ
7 ጁሙአ ሩፋኤል አሚን ወንድ ኦሮሞ ሉአላዊነትን በመፃረር ሞት ቃልቲ
8 ከዲር ሻኩር ሙሴ ወንድ ኦሮሞ ሽብር ሞት ቃልቲ
9 ሊቨን ዋሪዮ ጉዮ ወንድ ኦሮሞ ሽብር ሞት ቃልቲ
10 መላኩ ተፈራ ጥላሁን ወንድ ኦማራ ሽብር ሞት ቃልቲ
11 መስፍን አበበ አብዲሳ ወንድ ኦሮሞ ሽብር ሞት ቃልቲ
12 ሙሃመድ አህመድ አብዱላሂ ወንድ ሶማሌ ሽብር ሞት ቃልቲ
13 ሙሃመድ ሃሰን ሙሃመድ ወንድ ሶማሌ ሽብር ሞት ቃልቲ
14 ታደሰ ሃይሌ መኮነን ወንድ አማራ ሽብር ሞት ቃልቲ
15 ኡርጂ አበበ ቃበታ ሴት ኦሮሞ ሉአላዊነትን በመፃረር ሞት ቃልቲ
16 አብዱልራሺድ አብዱላሂም ወንድ ኦሮሞ ሽብር እድሜ ልክ ቃልቲ
17 አብዱራህማን ሙሳ ኢቶሳ ወንድ ኦሮሞ ሽብር እድሜ ልክ ቃልቲ
18 አብዱራህማን ኢሳ ሚቴሶ ወንድ ኦሮሞ ሽብር እድሜ ልክ ቃልቲ
19 አብዱራሺድ ባሺር ሁሴን ወንድ ኦሮሞ ሽብር እድሜ ልክ ቃልቲ
20 አበረ አሰፋ አበራ ወንድ አማራ ሽብር እድሜ ልክ ቃልቲ
21 አለሙ ጌትነት አባተ ወንድ አማራ ሽብር እድሜ ልክ ቃልቲ
22 አሊዩ ሙሚ ቦኮ ወንድ ኦሮሞ ሽብር እድሜ ልክ ቃልቲ
23 አማኑኤል ገመቹ ዱሬሳ ወንድ ኦሮሞ ሉአላዊነትን በመፃረር እድሜ ልክ ቃልቲ
24 አመራር ባይካል ካሳ ወንድ አማራ ሽብር እድሜ ልክ ቃልቲ
25 አንዱዓለም አራጌ ወንድ አማራ ህገመንግሥትን በሃይል መናድ እድሜ ልክ ቃልቲ
26 አሳምነው ፅጌ ወንድ አማራ ሽብር እድሜ ልክ ቃልቲ
27 ባካሪ ሙሃመድ አባሴና ወንድ ኦሮሞ ሽብር እድሜ ልክ ቃልቲ
28 ባሺር አህመድ መክታል ወንድ ኦሮሞ ለጦርነት መቀስቀስ እድሜ ልክ ቃልቲ
30 በላይ አበራ ጃቤና ወንድ ኦሮሞ ሉአላዊነትን መፃረር እድሜ ልክ ቃልቲ
31 ቦጋለ ጎንፋ ዋይሳ ወንድ ኦሮሞ ሉአላዊነትንመፃረር እድሜ ልክ ቃልቲ
32 ቸርነት የማነ ታደለ ወንድ አማራ ሽብርና ጦርነት መቀስቀስ እድሜ ልክ ቃልቲ
33 ዳኔል አያሌው ጮርቃ ወንድ አማራ ሽብርና ጦርነት መቀስቀስ እድሜ ልክ ቃልቲ
34 ደምሰው አንተነህ ደመላሽ ወንድ አማራ ሽብር እድሜ ልክ ቃልቲ
35 ደርጉ ኢቴና ገመቹ ወንድ ኦሮሞ ሉአላዊነትን በመፃረር እድሜ ልክ ቃልቲ
36 ዱላ ኦቲ ኦልጂራ ወንድ ኦሮሞ ህገመንግሥትን በሃይል መናድ እድሜ ልክ ቃልቲ
37 እማዋዪሽ ዓለሙ ወልደሚካኤል ሴት አማራ ሽብር እድሜ ልክ ቃልቲ
38 ፋይራ ኪቲላ ሳንካሌ ወንድ ኦሮሞ ሉአላዊነትን በመፃረር እድሜ ልክ ቃልቲ
39 ፋንታሁን ሙሃባ ሙፍቲ ወንድ አማራ ሽብር እድሜ ልክ ቃልቲ
40 ጌታቸው ብርሌ ደሴ ወንድ አማራ ሽብር እድሜ ልክ ቃልቲ
41 ገቱ ወርቁ ናደው ወንድ ጉራጌ ሽብር እድሜ ልክ ቃልቲ
42 ግርማ ረጋሳ ወይሳ ወንድ ኦሮሞ ሉአላዊነትን በመፃረር እድሜ ልክ ቃልቲ
43 ጎበና በላይ አየለ ወንድ አማራ ሽብር እድሜ ልክ ቃልቲ
44 ጎዳና ዳዩ ወንድ ኦሮሞ ሽብር እድሜ ልክ ቃልቲ
45 ጎሽራድ ጸጋው አጋፋሪ ወንድ አማራ ሽብር እድሜ ልክ ቃልቲ
46 ሃሊማ አብዲ ሞሃመድ ሴት ኦሮሞ ሉአላዊነትን በመፃረር እድሜ ልክ ቃልቲ
47 ሃሰን ሞሃመድ ሃሰን ወንድ ኦሮሞ ሽብር እድሜ ልክ ቃልቲ
48 ሁሴን ኡስማን ሳፋ ወንድ ኦሮሞ ሉአላዊነትን በመፃረር እድሜ ልክ ቃልቲ
49 ጃታኒ ኩኖ ቱንዳ ወንድ ኦሮሞ ሽብር እድሜ ልክ ቃልቲ
50 ካዲር ዝናቡ አባቡልጉ ወንድ ኦሮሞ ሽብር እድሜ ልክ ቃልቲ
51 ከበደ ግርማ ሁንዴ ወንድ ስልጤ ሽብር እድሜ ልክ ቃልቲ
52 ከፍያለው አብዲሳ ዱፈራ ወንድ ኦሮሞ ሉአላዊነትን በመፃረር እድሜ ልክ ቃልቲ
53 ክፍሌ ስንሻው ታደገ ወንድ አማራ ሽብር እድሜ ልክ ቃልቲ
54 ከፍያለው ተፈራ ደረሶ ወንድ ኦሮሞ ህገ መንግሥትን በሃል መናድ እድሜ ልክ ቃልቲ
55 ሊባን ዋሪዮ ጉዩ ወንድ ኦሮሞ ሽብር እድሜ ልክ ቃልቲ
56 መኮነን ወርቁ ዓለሙ ወንድ አማራ ሽብር እድሜ ልክ ቃልቲ
57 መንግስቱ አበበ አረጋዊ ወንድ አማራ ሽብር እድሜ ልክ ቃልቲ
58 መንግስቱ ሆርዶፋ ሙለታ ወንድ ኦሮሞ ሽብርና ጦርነት መቀስቀስ እድሜ ልክ ቃልቲ
59 መስፍን ኢታና ፉፋ ወንድ ኦሮሞ ሽብርና ጦርነት መቀስቀስ እድሜ ልክ ቃልቲ
60 ምስጋናው ተሰማ ተገኘ ወንድ አማራ ሽብር እድሜ ልክ ቃልቲ
61 ምስክር ካሳ ወንድም ወንድ አማራ ሽብር እድሜ ልክ ቃልቲ
62 ምትኩ ተስፋ ፋፋ ወንድ አማራ ሽብርና ጦርነት መቀስቀስ እድሜ ልክ ቃልቲ
63 ሞሃመድ ዳዲ ጃራ ወንድ ኦሮሞ ሽብር እድሜ ልክ ቃልቲ
64 ሞሃመድ ሁሴን ሞሃመድ ወንድ ኦሮሞ ሽብርና ጦርነት መቀስቀስ እድሜ ልክ ቃልቲ
65 ሙሳ ኡማር ዋዲያ ወንድ ኦሮሞ ሉአላዊነትን መፃረር እድሜ ልክ ቃልቲ
66 ሰይድ ሃሳን በሺር ወንድ ኦሮሞ ሉአላዊነትን መፃረር እድሜ ልክ ቃልቲ
67 ሰለሞን አሻግሬ አምበርብር ወንድ አማራ ሽብር እድሜ ልክ ቃልቲ
68 ጣሂር ሞሃመድ ኡስማን ወንድ ኦሮሞ ሽብር እድሜ ልክ ቃልቲ
69 ተማም ኢድሪስ አንቾ ወንድ ኦሮሞ ሽብር እድሜ ልክ ቃልቲ
70 ተመስገን ባይለየኝ ጸጋው ወንድ አማራ ሽብር እድሜ ልክ ቃልቲ
71 ተፈራ ማሞ ጨርቆስ ወንድ አማራ ሽብር እድሜ ልክ ቃልቲ
72 ተሻለ ሺፈራው ረጋሳ ወንድ ኦሮሞ ሉአላዊነትን በመፃረር እድሜ ልክ ቃልቲ
73 ፅጌ ሃብተማርያም ጮማሳ ወንድ አማራ ሽብር እድሜ ልክ ቃልቲ
74 ዋለልኝ ሃጢሶ ወንድ ሲዳማ ሽብር እድሜ ልክ ቃልቲ
75 ውድነህ ተመስገን ዓለሙ ወንድ አማራ ሽብር እድሜ ልክ ቃልቲ
76 ያሲን አዱኛ ዳባ ወንድ ኦሮሞ ሽብር እድሜ ልክ ቃልቲ
77 የሺዋስ መንገሻ በየነ ወንድ አማራ ሽብር እድሜ ልክ ቃልቲ
78 የሺዋስ ምትኩ ቸኮል ወንድ አማራ ሽብር እድሜ ልክ ቃልቲ
79 ይበልጣል ብርሃኑ ታፈረ ወንድ አማራ ሽብር እድሜ ልክ ቃልቲ
80 ዘይኑ አብዶ ተማም ወንድ ኦሮሞ ሽብር እድሜ ልክ ቃልቲ

 

ከላይ የተዘረዘሩትን እስረኞች አማራ፣ ኦሮሞ፣ ሶማሌ ጉራጌ እያሉ ማስቀመጡ ተገቢ ባይሆንም ወያኔ በዘር ላይ አነጣጥሮ እንደሚዘምት ማሳያ ይሆናልና አስፍላጊ ሆነ። ነገር ግን እነዚህ ሁሉ እስረኞችና በአጥቃላይ አገሪቱ ውስጥ የሚሰቃዩት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው። ቋንቋቸው፣ ሃይማኖታቸው፣ ፆታቸው፣ ሙያቸው የማንነታቸው መገለጫ አካል ቢሆንም ኢትዮጵያዊነታቸውን በልጦ የማንነት መታወቂያቸው ሊሆን አይችልም።

ወያኔዎቹ የህዝብ ጠላትነታቸው የሚታየው በማሰርና በመግደል ብቻ ሳይሆን በዘረፋም ነውና በዚህ መስክ ምን ያህል እንደተሰማሩ ትንሽ ማየት ያስፈልጋል።

የሃብት ዘረፋን በተመለከተ በተደጋጋሚ በብዙ ጸሃፊዎች፣ አክቲኢስቶችና ፖለቲከኞች ብዙ የተባለ በመሆኑ የዛሬ አጀንዳዬ አይደለም። መላ አገሪቷን የሚዘርፈው ወያኔ መሆኑን አዲስ አበባ ጥሩ ማሳያ ናት። ለኤርምያስ ለገሰ ምስጋና ይግባውና የምናውቀውን ተጨባጭ እውነት በአሃዝና በመረጃ እያስደገፈ በማቅረቡ የኢህአዴግን የፕሮፓጋንዳ ልሳን ሳይቀር እንዳይተነፍስ አድርጎታል። ወያኔዎች ከ1997 ዓ ም ምርጫ በኋላ በአዋጅ የአዲስ አበባን መሬት የቸበቸቡት በሃይለስላሴ፣ በግርማፅዮን በርሄ፣ በሃይሌ ፍስሃና በነጋ በርሄ መሪነት ቢሆንም ከዚያ በፊት ገና እንደገቡ ጀምሮ የመሬት ዘረፋው ላይ ያልተሰማራ ትልልቅ ባለስልጣን የለም። ሙት ወቃሽ አያርገኝና ጄኔራል ሃየሎም አርአያ በጓደኞቹ በተቀናበረ ተንኮል ቢገደልም፣ ከገዳዩ ጀሚል ያሲን ጋር በመሬት ጉዳይ ጠብ እንደነበራቸው በጊዜው በሚድያ ላይ የምንሠራ ሰዎች የምናውቀው እውነት ነው። ሃየሎምና የህወሃት መሪዎች የአዲስ አበባን መሬት መቸብቸብ የጀመሩት ገና በማለዳው ነው። ስለሆነም አባይ ፀሃዬ ቢንፈራግጥ አይገርመንም።

አቶ ሮባ መሃመድ “እነሱ ከተማቸው ላይ ኢንዱስትሪ እየገነቡ ለእኛ የተቆረጠ ጡት የያዘ ሃውልት ይገነቡልናል” ያሉትን መራራ እውነት ወያኔዎች በምንም መልኩ የሚያስተባብሉት አይደለም። ዛሬ ትናንት አይደለም። በትዕግስት ሲመለከታቸው የነበረ ህዝብ ዕድሉን በእጁ ብቻ እንደሚያገኝ በማመኑ ለመታገል የፖለቲካ ድርጅቶችና የካድሬዎች መሪነት አላስፈለገውም። እስር ቤቶች ሞልተው መፍሰስ ጀምረዋል። ፌደራሎችና አጋዚዎች የልብ ልብ ተሰምቷቸው ሰው የሚግድሉበትና የሚያሰቃዩበት ቀን ወደ ማብቃቱ ነው። ህዝቡ ይፈራ ነበር። አሁን የሚፈሩት የስርዓቱ አቀንቃኞችና ደጋፊዎቻቸው ሆነዋል።

ወያኔ የትግራይ ህዝብም ጠላት ነው

የተወሰኑ የትግራይ ልጆች ተሰባስበው የመሰረቱት የህወሃት ዋና አላማ የትግራይን ህዝብ ከአማራ ብሄር ነፃ ማውጣትና የትግራይ ሪፐብሊክን መመስረት እንደነበር ከራሳቸው ከህወሃቶች ጭምር ሲነገረን የኖረ ስለሆነ ሁሉም ያውቀዋል። ከሚናገሩትና ከሚጽፉት በላይ ግን የህወሃቶችን ድርጊት ላለፉት አርባ ዓመታት የተከታተለ ዓላማቸውን አጥርቶ ማወቅ ይችላል። ይህ ለትግራይ ህዝብ ጥቅም ቆሜአለሁ የሚለው ድርጅት እውነት ለትግራይ ህዝብ ቆሟል? ድርጊቱን እንመርምር።

ህወሃት ገና ጫካ ከመግባቱ ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ሃሳባቸውን የገለፁትንና ድርጅቱ ኢትዮጵያዊ አጀንዳ ይዞ እንዲታገል የጠየቁትን ጓደኞቻቸውን የትግራይ ልጆች በግፍ ገድለዋል። አባረዋልም። መሃሪ ዳዊት ከአዲግራት፣ እቁበእግዚዕ በየነ ከአክሱም፣ አስበሃ ዳኘው ከአድዋ፣ መንገሻ በላይ ከሽሬ፣ ሙሉጌታ አብርሃም ከእንደርታ፣ አልማዝ አስፋው ከመቀሌ፣ ኪዳኔ ግርማ ከመቀሌ፣ ተክሉ ሃዋዝ ከአድዋ ምን እንደተፈጸመባቸው ህወሃቶች ደፍረው ይናገራሉ?

በ1977 ዓ ም በነበረው ድርቅ ለትግራይ ህዝብ የተላከን እርዳታ ዘጠና ከመቶውን መሳርያ መግዣና የአመራሮች የውጭ ባንክ አካውንት ማበልፀያ በማድረግ በርካታ የትግራይ ገበሬዎች በርሃብ ተቀጥፈዋል።

አገራቸውን ከጠላት ተከላክለው ያዳኗትን የዮሃንስን፣ የአሉላንና የቀሪውን ጀግና የትግራይ ህዝብ ታሪክ ተፃርሮ የአገርን አንድነት አደጋ ላይ ጥሏል። ዮሃንስ የሞቱለት ድንበር ሳይቀር ለሱዳኖች ለመስጠት በመስማማት ላይ ነው።

ወያኔ ስልጣን ከያዘ ጊዜ ጀምሮ ጥቂት የትግራይ ልጆችን ከሌላው ኢትዮጵያዊ ለይቶ በመጥቀም ምስኪኑ፣ ብዙሃኑና ድሃው የትግራይ ህዝብ በሌሎች ኢትዮጵያውያን ዘንድ እንደልዩ ተጠቃሚና የስርዓቱ ደጋፊ ሆኖ በጥርጣሬ ዐይን እንዲታይ ሆን ብሎም እንዲቃቃር ሌት ተቀን እየሰራ ነው።

ወፋፍራሞቹ የወያኔ ድመቶች የሃይል ሚዛኑ ዘንበል ካለ እንደመንግስቱ ኃይለማርያም የያዙትን ይዘው ለመፈርጠጥ ቋፍ ላይ ናቸው። ግን የትም አያመልጡም። የፈሰሰው ደምና የተዘረፈው የአገር ሃብት የትየለሌ ስለሆነ በየሄዱበት ታንቀው ይጠየቁበታል። ወየው በስህተትም ይሁን ለጥቅም ብለው ወያኔን ለሚደግፉ አድርባዮች! ታዝዘን ነው የሚለው ምክንያት የደርግ ባለስልጣናትን በእስር ከመበስበስ አላዳናቸውምና።

ወየው በስሙ ለተነገደበትና ከወንድሞቹ ኢትዮጵያውያን እንዲቆራረጥ እየተገፋ ላለው የትግራይ ህዝብ!! ሻዕብያና ወያኔ አቅል ባጡበት ፍቅራቸውና ኋላም በጠባቸው ጊዜ በሰሩት ስህተት ምስኪኑ የኤርትራ ህዝብ ከኢትዮጵያውያን ወንድሞቹ መለያየት ብቻ ሳይሆን እስከአሁን ለአለበት ዳፋ እንደተዳረገው ወያኔዎች ለትግራይ ህዝብ ያዘጋጁት ይህንኑ ዕድል ነው።

ትዝብት ይሁን ድምፃቸውን ላጠፉት የትግራይ ምሁራን። አንድም የሚደርሳቸው የዘረፋ ጥፍጣፊ፣ አንድም አደባባይ ያላወጡት ዘረኝነት ተፈታትኗቸው አንደበታቸው ተዘግቷል። ከገብረመድህን አርዓያ፣ ከአብርሃ ደስታና ከአስገደ ግብረስላሴ ውጭ ሌሎች የት ገቡ? ወያኔ ኢትዮጵያን በተለይም የትግራይን ህዝብ ህልውና ሊያጠፋ ሉአላዊነቷና ዜጎቿ ላይ ሲነሳ፣ በህዝብ ደም እጁን ሲታጠብ የት ነበርን ሊሉ ነው? አፋቸውን በእጃቸው ከድነው ሲስቁ እየታዩኮ ነው!

ወያኔ በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላት ነው!

• ኢትዮጵያን ያለህዝብ ፍላጎትና ውሳኔ ያለወደብ ያስቀረ፤
• ከሰማንያ ሺህ በላይ ዜጎቿን በማይረባ ጦርነት ማግዶ ካስጨረሰም በኋላ ያለመፍትሄ ያስቀመጠ፤
• ጋምቤላ፣ አሰቦት፣ አርባጉጉ፣ ወተር፣ ጎንደር አደባባይ ኢየሱስ፣ አሶሳ፣ አረካ ወላይታ፣ አዋሳ፣ አፋር፣ አዲስ አበባና አሁን ደግሞ በመላ ኦሮምያና ጎንደር ኢትዮጵያውያንን የጨፈጨፈና ያስጨፈጨፈ፤
• አባቶቻችን በመስዋዕትነት ዳር ድንበሯን ያስጠበቋትን አገር ለሱዳን ለመስጠት ያልሳሳ፤
• ድሃ ገበሬን እያፈናቀለ ለህንድ፣ ለአረብ፣ ለቻይና መሬት በነጻ ያደለ፤
• የአገሪቱን ሃብት ጠቅልሎ በወያኔ ካምፓኒ ኤፈርት ቁጥጥር ስር ያዋለ፤
• የአገሪቱን ወጣት ሴቶችን ለአረብ፣ ወታደሮችን ለአሜሪካ ቅጥረኝነት፣ ህፃናትን ለምዕራቡ ገበያ አውጥቶ የቸበቸበ፤
• አገሪቱን ፍትህ አልባ አድርጎ ዜጎችን ሙሉ በሙሉ ወደ እስረኝነት የለወጠ፤
• ኢትዮጵያውያንን በዘር ከፋፍሎ ለህልውናችን በአንድነት እንዳንቆም አድርጎ ለአለንበት ውድቀት የዳረገን፤
• ሚሊዮኖች ተርበው “የተራበ የለም” የሚልና ሲጋለጥ ደግሞ በርሃቡ ላይ እንዳይተኮር ጠንክሮ የሚሠራ ጨካኝና ዘረኛ ቡድን መሆኑን ያልተሀነዘበ ኢትዮጵያዊ ካለ ጤነኛ አይደለም። የህወሃት ወፍራም ድመቶች አፋቸውም፣ እጃቸውም ደም በደም መሆኑን ኢትዮጵያዊ ብቻ ሳይሆን ዓለም አይቷል። መደበቂያ የላቸውም።

ሌሎችን በማጥፋት ራሱን ያገዘፈው ወያኔ ከሁሉም አቅጣጫ በህዝቡ በሚሰነዘር ጥቃት በመድማት ላይ ያለ የቆሰለ አውሬ ሆኗል። ደም አስክሮት እየተወራጨ ነው። መድማቱን የሚያቆምበት ፋታ አጥቷል። አለኝታ ያጣው ህዝብ በቃኝ ብሎ በመነሳት የሚወረውራት እያንዳንዷጥቃት የወያኔን ሞት እያፋጠነችው ነው። ከተመልካችነትና ከአሽሟጣጭነት ወጥቶ የህዝቡን ትግል መቀላቀል አሁን ነው። ወያኔ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ጠላት ስለሆነ የመውደቁ ድል የጋራ እንዲሆን ትግሉም የጋራ ሊሆን ይገባል።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ በሙሉ!

 


አንተነህ መርዕድ - ፌብሩዋሪ 17 ቀን 2016

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ