የጥላቻ-ፖለቲካ ለኢትዮጵያ ህልውና ጠንቅ ነው (ከአብርሃም ያየህ)
ከአብርሃም ያየህ (ሐምሌ 30 ቀን 2000 ዓ.ም. / August 6, 2008)
ባሁኑ ጊዜ፣ በኢትዮጵያ የቃሚዊው ጎራ፣ የአብዛኛዎቹ ተቃዋሚ ነን ባይ ኃይሎችና ደጋፊዎቻቸው ዋነኛ የማታገያ ስልት ሆኖ በማገልገል ላይ ያለው በጥላቻ የተመሰረተ ፖለቲካ ነው። ይህ መርዘኛና አደገኛ የጥላቻ-ፖለቲካ፣ በትግራይ ስም በሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ወይም በገዢው ፓርቲ ብቻ ያተኮረ አይደለም። አትኩሮቱ፣ በጅምላ አጠቃላዩን የትግራይ ህዝብ ዒላማ ያደረገ ነው። የህዝባቸውና ያገራቸው ህልውና የሚከነክናቸው ዜጎች፣ የዚህ አደገኛ በሽታ መዘዙ በትክክል ተረድተው አጥብቀው ካልታገሉት በቀር፣ ሄዶ-ሄዶ በመጨረሻ ኢትዮጵያን በመበተን ያለው ሚና እጅግ ወሳኝ ነው።
ጥላቻ አንድ ራሱ የቻለ ከባድ በሽታ ብቻ ሳይሆን፣ የብዙ በሽታዎች ምንጭ ጭምር ነው። አንድ ሰው አንዴ በዚህ በሽታ ከተለከፈ ደግሞ ከበሽታው በቀላሉ ለመፈወስ ቀላል አይደለም። ይህ ፀረ-ትግራይ ህዝብ የሆነ በጥላቻ የተመሰረተ የፖለቲካ በሽታ ጥልቀቱና ስፋቱ ምን ያህል እንደሆነ ከማመላከቴ በፊት፣ ጥላቻ የሚያስከትለውን አደገኛ ስቃይ የሚያሳይ አንድ አስገራሚ ገጠመኝ አንባቢዎቼን ለማጋራት እሻለሁ። (ሙሉውን በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)



