ኢትዮጵያውያን ብቻ የሚያስወግዱት አረም
አብራሃም ለቤዛ

እንቦጭን ከጣና ወያኔን ከአፋር ላይ ነቅለን የጣልን ለት፤
የባህርዳር ፈርጥሽ የአፋር ገሞራ አለት፤
ታትሞ ይቀራል በዓለም-አቀፍ መዝገብ ይሆናል ቅርስ ውበት፤
መቼ ይጎልና አሳውም ከጣና በከል ወተቱ አፋር ቤት፤
ሕብረታችን ይታይ አንዱ ለአንዱ ይድረስ፤
ዋጋ ያስከፍላል መታገስ እኛ ዘንድ አስቲደርስ።
የማሕበራዊ ልማት ልማት አጥኝዎች ጥናቶቻቸውን ተደራሽነት ለመጨመር የገጠሩን ማሕበረሰብ አሳታፊ የሆነ የጥናት መንገድ (Participatory Rural Appraisal) መጠቀምን ይመክራሉ። እነዚህ የጥናት መንገዶች ተግባራዊ ማደረግ ለጥናታችን ግብዓት የሚሆነን መረጃ ማንበብና መጻፍ ከማይችለው (However, literacy and numeracy are quite different) የማሕበረሰብ ክፍል ለጥናታችን ግብዐት የሚሆነንን መረጃ በአግባቡ ለማግኘት ያግዘናል። ለጥናታችን ግብዓት መረጃ ማግኘታችን ለጥናታችን የመፍትሄ አቅጣጫ ለማመላከት የራሱ ጉልህ አስተዎጽኦ አለው።
የገጠሩን ማሕበረሰብ አሳታፊ የሆነ የጥናት መንገድ (Participatory Rural Appraisal) ውስጥ ለወሳኝ ክስተቶች መረጃ ማግኛ ዘዴ (Timeline/Historical Mapping) አንዱ ሲሆን፤ የማሕበራዊ ልማት ልማት አጥኝዎች በጥናታቸው አካባቢ ወደ ሆላ ተጉዘው ምን ምን ክስተቶች እንደነበሩ የጥናቱ ተሳታፊዎችን የሚጠይቁበት መንገድ ነው።
ከላይ ያለውን ሃተታ ያነሳሁት በአፋር ክልል ላይ ስለተከሰተው “PROSOPIS” የተባለ አረም የማሕበራዊ ልማት አጥኝዎች የተቸገሩበትን ጉዳይ ስላየሁ ነው። ይህ ዓረም ወያኔ እየተባለ በአፋር ነዎሪዎች ዘንድ የሚታወቅ ቢሆንም፤ አንዳንድ የማሕበራዊ ልማት አጥኝዎች የጥናት ወረቀቶች ስመለከት ደርጊ እያሉ በጥናታዊ ፅሁፋቸው ገልጠውታል። በአፋር የሚገኘው ወያኔ የተባለው አረም ከወያኔ ጋር አብሮ መጣ ብለው ስለሚያምኑ እና ለ26 ዓመት በአፋር የሚገኝ ሆኖ በአርብቶ አደሩ የግጦሽ መሬት ላይ ወረራ በማካሄድ ለአርብቶ አደሩ የራስ ምታት ሆኖበታል። እንቦጭ በጣና ስንት ዓመት ሆኖት ይሆን?
ብዙ ብር ወጥቶባቸው ጥናት የምታደርጉ ተቋማት ወደ እውነታው ተመለሱ። ጥናት ማድረግ ሌላ፤ ፖለቲካ ሌላ ነው የእኔ መልዕክት። የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ደግሞ በእንግሊዘኛ መጠቀም መርጠዎል (http://www.ena.gov.et/index.php/economy/item/11520-2017-02-05-17-32-42)። ምናልባት የመገናኛ ብዙሃን ሪፎርም እየተዘጋጀ ነው ተብሎ የተራገበለት ይኽን ይቀርፍ ይሆን? አብረን እናያለን።



