Bekele Gerba

አቶ በቀለ ገርባ

አምባቸው ደጀኔ

አገራችን በየቀኑ መነጋገሪያ አጀንዳ አታጣም - በተለይ በዚህ ዘመንና በጣም በተለይ ደግሞ ባለፉት 12 ወራት። በነዚህ ሁለት ቀናት ደግሞ “አትርሱኝ” እያለ ያለው በቀለ ገርባ ነው።

ላለመረሳትና በሕዝብ አንደበት ዘወትር ለመወሳት እኮ በግድ ክፉና ጠማማ መሆን አያስፈልግም። ሰዎች እንዴት ነው እያሰቡ ያሉት? እንዴትስ ነው ያድጋሉ ሲባሉ እያነሱና እየኮሰመኑ የሚሄዱት? ምን ቢነካቸው ነው? አንድ ሰው ዕውቀትንና ጥበብን መጨመር ቢያቅተው ያለውን ይዞ መጓዝ እንዴት ይሳነዋል?

በቀለ ገርባ - አሁን ‘በቀለ ገሪባ’ ብለውም ሲያንሰው ነው - ‘ገሪባ’ ማለት ታዲያን ዕውቀት የሚጎድለው ባላገር ሰገጤ ማለት እንደሆነ ልብ ይባልልኝ - በትልቅ የትምህርት ተቋም በመምህርነት ብዙ ጊዜ አገልግሏል። ያስተማራቸው ወጣቶችም ኢትዮጵያውያን እንጂ ከአንድ ጎሣ ተመርጠው የገቡ አይመስለኝም። ኢትዮጵያ ያለቻቸው ጎሣዎች ደግሞ ከ85 በላይ እንጂ ኦሮሞ ወይም አማራና ትግሬ ብቻ አይደሉም። በዚያ ዐይነት የትምህርት መድረክ የነበረ ሰው ዘረኝነትን ሊጠየፍና ኮዝሞፖሊታን አስተሳሰብ ሊላበስ ሲገባው፤ እንደ አንድ ተራ ያልተማረ ዜጋ የዘረኝነት አዘቅት ውስጥ ተዘፍቆ ሲርመጠመጥ ማየት እጅግ ከማሳዘኑም በላይ ለሰውየው ለራሱ ማዘንም ተገቢ ነው፤ በቁም ለሞተ ሰው ማዘን ነግ በኔን ማሰብ ስለሆነ። ኢትዮጵያ እንደሆነች በቀለ ያን አለ ይህን አለ የምትሆነው የለም። እንኳንስ የበቀለ ከፋፋይ የዘረኝነት ንግግርና ስብከት፤ መለስ ዜናዊና ዓለም አቀፉ የኢሉሚናቲ ፀረ-አቢሲኒያ ኃይላት ከ300 ዓመታት ለበለጠ ጊዜ ፈግተው ኢትዮጵያን አላፈረሷትም፤ በፈጣሪ ጥበቃ ሥር ስላለችም ትንገዳገዳለች እንጂ አትወድቅም። ይህ ብቸኛው ኢትዮጵያዊ ሐቅ ተፈጥሯዊና መለኮታዊ የማይሻር ሕግ መሆኑን ለመረዳት የአገራችንን ታሪክ ልብ ብሎ ማጤን ነው።

በቀለን ግን ምን ነካው?

ይልቁንስ ስለዶክተር አንጋሣና መሰል የኦሮሞ አክቲቪስቶች የተሰማኝን ልዩ ኩራትና የአለኝታነት ስሜት በዚህች አጋጣሚ ልግለጽላችሁ። ያየሁት ትናንት ነው። አንድ ወጣትና ዶ/ር አንጋሣ በዩቲዩብ እየተናገሩ የሰማሁት ነገር በደስታ አሰከረኝ። የሚናገሩት ስለኦነግ ነው። በመቀመጫው ነው ቁጭ ያደረጉት። ፈልጉና አዳምጡት። የእናት ሆድ ዥንጉርር መባሉ ለዚህ ነው። እነበቀለ ቀርባና ጃዋር መሐመድ በተፈጠሩበት የኦሮሞ ኢትዮጵያውያን ግዛት ቶሎሣ ኢብሣንና ዶ/ር አንጋሣን፣ ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሣንና ሌሎችንም ብርቅዬና ውድ የኦሮሞ ልጆች ስናይ፤ ውኃ እንዳገኘ የበረሃ ተክል ተስፋችን ይለመልማል፤ ሕልማችንም እንደጽጌረዳ ያብባል። ተባረኩልኝ። ልጅም ይውጣላችሁ። በተቃራኒው ኢትዮጵያን ለማፍረስ የምትቃትቱ ወንድሞቼና እኅቶቼ ጥቁር ውሻ ውለዱ።
የነበቀለ ገርባ ጉዳይ ግን በተከድኖ ይብሰል ብቻ የሚተው አይደለም። ዘመድ ለመቼ ነው? አክስት አጎት ለመቼ ነው? ወዳጅ ጎረቤትስ ለመቼ ነው? ሳይብስባቸው በሰንሰለት አስሮ ወደሚቀርባቸው ጠበል መውሰድና የተሣፈረባቸው ወያኔያዊ የአጋንንት መንጋ እስኪለቃቸው ድረስ ማስጠመቅ ነው። የወሊሶው አባ ወልደትንሣኤ በሕይወት ቢኖሩ ኖሮ ይሄኔ ስንቱን የዲያብሎስ ጭፍራ ከአገራችን ያስወጡልን ነበር። ወይ ነዶ!

 

አንድ ሰው ካላበደ ወይ ካልሰከረ እንዲህ ያለ ማፈሪያ ነገር አይናገርም። ግን ምን ነካው?

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!